አረና ትግራይና ትዴፓ በትግራይ ክልል ምርጫ አንሳተፍም ሲሉ ዳግመኛ ገለጹ

አረና ትግራይና ትዴፓ በትግራይ ክልል ምርጫ አንሳተፍም ሲሉ ዳግመኛ ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በህወሓት ጡረተኛ ነባር ታጋዮች የሚዘወረው የትግራይ ክልል ከቀሪው የአገሪቱ ክፍል በተለየ በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ ክልላዊ ምርጫ አካሂዳለሁ ቢልም በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ፓርቲዎች ግን በምርጫው አንሳተፍም ማለታቸው ተሰማ።

ይካሄዳል እየተባለ በሚፎከርበት  ምርጫ ላይ  ህወሓት፣ ሳልሳይ ወያኔ፣ ባይቶና ትግራይ እና የትግራይ ነጻነት ድርጅት (ሦስቱም ድርጅቶች የህወሓት ተለጣፊ ናቸው)
ቢሆኑም፤ በክልሉ የላቀ ተሰሚነት ያላቸው አረና ትግራይ እና የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲዎች አሁንም በምርጫው ለመሳተፍ በያዙት አቋም መግፋታቸውን ገልጸዋል።
ህወሓት ብቻውን ተወዳድሮና ቀለብ በሚሰፍርላቸው ጀሌዎቹ  ታግዞ ዳግም በምስኪኑ የትግራይ ሕዝብ ላይ ለመፈንጨት በቋመጠበት ምርጫ ላይ እንደማይሰተፍ አረና ትግራይ ፓርቲ በድጋሚ አስታውቋል።
 በክልሉ የሚካሄደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት የለኝም ያለው  የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ፤ በክልሉ የሚካሄደው ምርጫው ሕጋዊ ነው ብለው እንደማያምኑና ፓርቲያቸውም እንደማይሳተፍ ገልጸዋል።
በአንጻሩ የምርጫ ሕጉንና ደንቡ፣ እንዲሁም ኮሚሽኑን በማቋቋም ወቅት የአካሄድ ችግር አስተውለናል በማለት ለቢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡት በክልሉ በሚካሄደው ምርጫ ላይ የሚሳተፉት ፓርቲዎች ለይስሙላ “ህወሓት ባለቀ ነገር ላይ ፣ በስተመጨረሻ ነው የጠራን” ሲሉ ነገሮች በምስጢር የተከናወኑ ለማስመሰል ሞክረዋል።
 የአሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዶሪ አስገዶም በበኩላቸው፤ ድርጅታቸው በመጪው ነሐሴ ይካሄዳል ተብሎ በተቀጠረው ክልላዊ ምርጫ እንዳይሳተፍ እየተገለለ እንደሆነ ጠቁመው፤ በተለይም የምርጫ ሕግና የምርጫ ኮሚሽን ለማቋቋም በተደረገው ውይይት ላይ እንዳንሳተፍ ተደርገናል ብለዋል።
ህወሓት ከሚፈልጋቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ምርጫውን ለማካሄድ ነው የሚፈልገው የሚሉት ሊቀመንበሩ፤
የአሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ለኢሮብ ሕዝብ ለመታገል የተቋቋመ መሆኑንና ክልላዊ ምርጫው መካሄድ አለበት ብሎ እንደሚያምንም አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY