በቦረና ዞን የሕክምና ባለሙያዎች 50 ኪሎ ግራም ፕላስቲክ በቀዶ ሕክምና አወጡ

በቦረና ዞን የሕክምና ባለሙያዎች 50 ኪሎ ግራም ፕላስቲክ በቀዶ ሕክምና አወጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን 6 የእንስሳት ሐኪሞች ከአንዲት ላም ሆድ ውስጥ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ በቀዶ ሕክምና አውጥተዋል ተባለ።

ላሟ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ከቀዶ ጥገናው በኋላ የተናገሩት ዶክተር ፍራኦል ዋቆ፤ “ከብቶች የሚግጡት ሳር ሲያጡ ወይም በሰውነታቸው ውስጥ የንጥረ ነገር እጥረት ሲያጋጥማቸው ፕላስቲክ ሊበሉ ይችላሉ” ሲሉ ተደምጠዋል።
ሰዎች ፕላስቲክ የሚያስወግዱበት መንገድ ለቁም እንስሳት ጤና ችግር እየፈጠረ ነው ያሉት የሕክምና ባለሙያው፤ 50 ኪሎ ግራም ፕላስቲክ የተወገደላት ላም ባለቤት የሆኑት አቶ አሬሪ ጨሪ፣  ቀደም ሲልም ፕላስቲክ የተመገበች ሌላ ላም ወደ ጤና ባለሙያዎቹ ወስደው 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ ከሆዷ እንደወጣላት አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY