በአዲስ አበባ በዘንድሮው መርሀ ግብር እስካሁን ዐራት ሚሊዮን ችግኝ ተተክለዋል...

በአዲስ አበባ በዘንድሮው መርሀ ግብር እስካሁን ዐራት ሚሊዮን ችግኝ ተተክለዋል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በዛሬው ዕለት በእንጦጦ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

እስካሁን በከተማዋ ከ4 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና፤ በከተማዋ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ይፋ አድርገዋል።
ሓላፊዋ በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን እና በከተማዋ እየተከናወኑ ስላሉ የችግኝ ተከላ ሂደቶችን በተመለከተ ሠፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የብዝኃ ሕይወትን በመጠበቅና ጅምር ሥራዎችን በማጠናቀቅ አዲስ አበባ ለሁሉም ምቹ ከተማ እንድትሆን እንሠራለን ያሉት አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ፣ በ2012 ዓ.ም የክረምት ወቅት ይተከላል ተብሎ ከታቀደው 5 ቢሊዮን የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር 7 ሚሊየን ችግኝ በአዲስ አበባ የሚተከል ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በቅርቡ በአጠቃላይ 28 ሚሊየን ብር የሆነ የወር ደምዎዛቸውን ለግድቡ ግንባታ እንዲውል መስጠታቸውን የጠቆሙት አቶ የፓርቲው ጽ/ቤት ሓላፊው፤ የግድቡ የመጀመሪያ ዙር ውሀ ሙሌት በድል መጠናቀቅ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ለመውሰድ የጀመርነውን ጉዞ ማሳካት እንደሚቻል ያሳየንበት ነው ሲሉም ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY