የፌደራል መንግሥትና የብልፅግና አመራሮች ከትግራይ ባለሀብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ተወያዮ

የፌደራል መንግሥትና የብልፅግና አመራሮች ከትግራይ ባለሀብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ተወያዮ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፌደራል መንግሥት፣ የብልጽግና ፓርቲና የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ  አመራሮች ፤ ከትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዮ።

“የፌደራል መንግሥት ጦርነት ሊከፍትብን ነው፣ መንግሥት የትግራይ ክልልንና ተወላጆችን እያገለለ ነው” የሚሉ የፕሮፖጋንዳ ትርክቶች ለፖለቲካ ፍጆታ ከመዋላቸው ባለፈ፣ በመሬት ላይ የሌሉ መሆናቸውን ከተወያዮቹ ጋር በመተማመን ላይ መደረሱ ተነግሯል።
በማንኛውም ዘርፍ በህጋዊ መንገድ ልማትና የሀገር እድገት ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ የትግራይ ባለሀብቶች መንግሥት ከጎናቸው እንደሚቆም ቃል እንደተገባላቸው የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታውቋል።
በዚህ መሠረትም ጉዳዮን እየተከታተለ የሚያስፈፅም ተወካዮች መሰየማቸውም ተሰምቷል።
“አገር ሊፈርስ ነው ጓዝህን ጠቅልለህ ወደ ክልልህ ግባ ” በሚለው የህወሓት ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ሳይታለሉ ራሳቸውን አረጋግተው ሊሠሩ እንደሚገባም ለባለሀብቶቹ ተገልጿል።
 ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ናት፤ ሁላችንም ሠርተን የምንለወጥባት ሀገር እንጂ የምንሸማቐቅባት ሀገር አለመሆንዋንም መገንዘብ ያስፈልጋል ያሉት የብልፅግና ፓርቲ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣናት የትግራይ ባለሀብቶች ለተሻለ ግንባታና የፈጠራ ሥራ እንዲበረታቱ እንደሚደረግም ገልጸዋል።
SHARE
Previous article
Next article

LEAVE A REPLY