ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌደራል ፖሊስ አባላት መከበቡን ተከትሎ ቦሌ የሚገኘው የግለሰቡ ቤት አካባቢ ብጥብጥ ለማስነሳት የሞከሩ መንጋዎች፣ የኦነግ አባላትና ደጋፊዎች በሪፐብሊካን ጦር እንዲበተኑ ተደረገ።

ዳውድ ኢብሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ሊውሉ እንደሚችሉ የተገመተበትና መኖሪያ ቤታቸው መከበቡን የጠቆመው ዜና ከሰዐታት በፊት መሰራጨቱን ተከትሎ በርከት ያሉ መንጋዎች በአካባቢው ላይ ቀስ በቀስ መጠራቀማቸውን የጠቆሙት ታማኝ የዜና ምንጮቻችን፤ እነዚህ ኃይሎች ወደ አቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት ካልተጠጋን በሚል በስፍራው ከሚገኙ የፌደራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ጋር ግርግር ለመፍጠር መሞከራቸውን ይፋ አድርገዋል።
በአካባቢው ችግር ለመፍጠር የሞከሩትን የኦነግ ደጋፊዎችና የመንጋ ፖለቲካ አራማጆችን ከኦነጉ ሊቀመንበር መኖሪያ ቤት በተወሰነ ርቀት ላይ በፖሊስ እንዲገደቡ የተደረገ ቢሆንም፤ ምሽቱ እየተቃረበ መሄዱን ተከትሎ ኹከት እንዳይፈጠር በማሰብ፣ የሪፐብሊካን ጦር አባላት ከ30 ደቂቃ በፊት በቦታው በመገኘት ግርግር የናፈቀውን ኃይል እንዲበተን አድርገውታል።
በጃዋር መሐመድ የ”ፈሪ” ጥሪ ተከስቶ የነበረው ዓይነት ኹከት ለመፍጠር የቋመጡ ኃይሎችን ወደመጡበት የመለሰው የሪፐብሊካን ጦር በአሁኑ ሰዐት ሙሉ ለሙሉ አካባቢውን ተቆጣጥሮታል።

LEAVE A REPLY