ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድ ያላቸውን ድጋፍ ያሳዮበትን ለኖቤል የሰላም ሽልማት ኮሚቴ ደብዳቤ አስገብተዋል ተባለ።
ኑሮአቸውን በኖርዌይ ያደረጉና በተለያዩ ተቋማት ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፤ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ አስመልክተው ደብዳቤውን እንዳስገቡ ተሰምቷል።
የኦሮሚኛ ሙዚቃ ድምጻዊው ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ የተፈጸመውን ድርጊት በማውገዝ፤ የመንግሥትን የሰላም ጥረት ለማደናቀፍ የተደረገ ሴራ መሆኑን በደብዳቤያቸው ያመላከቱት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የሀገሪቱን እድገት እና ብልጽግና ለማረጋገጥ ሌት ተቀን እየሠሩ ይገኛሉ ሲሉም ለኖብል ሽልማት አዘጋጅ ኮሚቴው አሳውቀዋል።
ኮሚቴው የኢትዮጵያ መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት ሊገነዘብ ይገባዋል ያሉት ድጋፍ ሰጪ ኢትዮጵያውያኑ፤ ኮሚቴው ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የሰጠው የሰላም የኖቤል ሽልማት ትክክለኛና የሚገባቸው መሆኑን እናምንበታለን ሲሉም ማረጋገጫቸውን ሰጥተዋል።