በደቡብ ክልል በዛሬው ቀን ብቻ 70 ሚሊዮን ተተክሏል ሲሉ የመንግሥት ሚዲያዎች ተናገሩ

በደቡብ ክልል በዛሬው ቀን ብቻ 70 ሚሊዮን ተተክሏል ሲሉ የመንግሥት ሚዲያዎች ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ሁሉም አካባቢዎች ዛሬ ብቻ ከ70 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል ተባለ።

የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሓላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፤ ዛሬ በሁለተኛው ዙር የክልሉ በጋራ ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር ላይ፣ በጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ ካራሶዲቲ ቀበሌ በመገኘት ከሀገር ሽማግሌዎችና ከግብርና ሚኒስቴር ከመጡ አመራሮች ብሎም ከሕዝቡ ጋር ችግኞች መተከላቸውን ገልጸዋል።
የክልሉ ግብርና ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ  እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ በዓመቱ ከታቀደው 5 ቢሊየን ችግኝ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ መተከሉን አስታውሰው፤ በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎችም ለአረንጓዴ አሻራው መሣካት ሁሉም የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ አስረድተዋል።
በመንግሥት ሚዲያዎች በኩል ዛሬ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች በሙሉ በክልሉ በዛሬው ዕለት ብቻ ከ4 ሚሊየን በላይ ሕዝብ በችግኝ ተከላው መሣተፉንና 70 ሚሊዮን ችግኝ መተከሉን ቢናገሩም፤ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መቀመጫቸውን ያደረጉ ዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ተተከለ ስለተባለው አኃዝም ሆነ ስለ ችግኝ መርሀ ግብሩ ያሉት ነገር የለም።

LEAVE A REPLY