የ12ኛ ክፍል ዓይነ ስውራን ለአምስት ቀናት የቴክኖሎጂ ሥልጠና ሊሰጣቸው ነው

የ12ኛ ክፍል ዓይነ ስውራን ለአምስት ቀናት የቴክኖሎጂ ሥልጠና ሊሰጣቸው ነው

Federal Democratic Republic of Ethiopia - vector map

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ለሚፈተኑ ተማሪዎች በኦላይን እንዲፈተኑ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረገ ነው ተባለ።

በተመረጠው መንገድ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች በኦን ላይን ለመፈተን ከባድ ስለሚሆንባቸው፤ ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከተስማሚ ቴክኖሎጂ ማዕከል  ጋር በመተባበር ለአምስት ሳምንት የሚቆይ ስልጠና እንዲሰጣቸው መታቀዱም ተሰምቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት  የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፤ የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን እንደሚሆን እና ለዚህም አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አረጋግጠዋል።
የኦን ላይን ፈተና አሰጣጡ ዓይነ ስውራን ተማሪዎችን የሚያካትት በመሆኑ ለእነርሱ የቴክኖሎጂ ሥልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን እናምንበታለን ሲሉም ተደምጠዋል።
 በዚህ በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ፣ በተመሳሳይ ከ12ኛ ክፍል ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እና ዝግጅት እንደሚደረግ የተናገሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሠው ወልደሃና፤ ለዘንድሮ ማትሪክ ተፈታኝ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች የቴክኖሎጂ ሥልጠና ለመስጠት እና ለማገዝ  የኒቨርሲቲው ድጋፍ እንዲደርግ በመደረጉ ደስተኞች ነን ብለዋል።

LEAVE A REPLY