ኦነግ ለሁለት ተሰነጠቀ፤ “ጉሚ ሰባ” (የአመራሮቹ ጉባዔ) እውቅና የለውም ተባለ

ኦነግ ለሁለት ተሰነጠቀ፤ “ጉሚ ሰባ” (የአመራሮቹ ጉባዔ) እውቅና የለውም ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ለሁለት መከፈላቸውና ሊቀመንበሩን ያወረደው “ጉሚ ሰባ” የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባም እውቅና እንዳልነበረው ተሰማ።

ግንባሩን ሲመሩ የነበሩት ጃል ዳውድ ኢብሳ ከሥልጣን እንዲወርዱ ተደርገዋል ቢባልም፤ እርሳቸውን እንዲተኩ ተመርጠዋል የተባሉት አቶ አራርሶ ቢቂላ ወሬው  ሐሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል።
ትናንት በኦነግ ጽሕፈት ቤት የተካሄደው ምርጫ፤ የሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ እውቅና ነበረው ያሉት አቶ አራርሳ አሁንም የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
“በዋና አጀንዳነት ሕዝቡ ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል? ድርጅታችንስ ምን ድረጃ ላይ ነው? ወደ ሀገር ከገባን በኋላ ምን አገኝን፣ ምን አጣን? የሚለውን በጉባዔው ገምግመናል” ያሉት አቶ አራርሳ ቢቂላ፤  በአሁኑ ጊዜ የታሰሩ የግንባሩ አባላት እና አመራሮችን በተመለከተ ተሳታፊዎች  አንድ ዓይነት ሐሳብ ይዘን ወጥተናልም ብለዋል።
 የግንባሩ ሊቀ መንበር በከተማው ውስጥ እያሉ፣ በሚመሩት ድርጅት ስብሰባ ላይ ሳይገኙም ፤ ውይይቱን ስለማድረጋቸው የተጠየቁት አዲስ ተመራጭ ሊቀመንበሩ፤ “አቶ ዳውድ የተለየ ጉዳይ ስለገጠማቸው እየተንቀሳቀሱ የዕለተ ከዕለት ሥራቸውን ማከናወን ባለመቻላቸው ስብሰባችን ላይ መገኘት አልቻሉም። ይሁን እንጂ ስለ ጉዳዩ ከጃል ዳውድ ጋር ተነጋግረንበት ነበር።” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የትናንቱ ስብሰባ እንዲካሄድ የሊቀ መንበሩን ይሁንታ እንዳገኘ ያመላከቱት ከፍተኛ አመራሩ፤ ውይይታችንን ሳንጨርስ ኔትዎርክ ተቋርጦ ነበር። ነገር ግን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር “ጉሚ ሰባ”  ተሰብስቦ እንዲመክር ተስማምተን  ስለነበር፣ ዋናው ሊቀ መንበር ባለመገኘታቸው በምክትሉ የሚመራ ዓይነት ሰብሰባ ቢካሄድም ምንም አይነት ሹም ሽር እንዳልተካሄደ ገልጸዋል።
ትናንት በሊቀመንበርነት ተመርጠዋል የተባሉት አቶ አራርሶ ቢቂላ ይህንን ቢሉም፤ የኦነግ ቢሮ ሓላፊ የሆኑት ዶክተር ገዳ ኦልጅራ “ትናንት በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ሰብሰባ የድርጅቱ እውቅና የለውም። ስብሰባው በግንባሩም ሆነ በሊቀ መንበሩ የማይታወቅ ነው” ሲሉ በድርጅቱ ውስጥ መከፋፈል መኖሩን ያመላከተ ምላሽ ሰጥተዋል።
አዲስ ተሿሚው አቶ አራርሶ፤ ከአቶ ዳውድ ስብሰባ ለማካሄድ ፍቃድ እንደተሰጣቸው በመናገር ስብሰባ ሲጠሩ፤ ዶክተር ገዳ ወደ አቶ ዳውድ ስልክ ደውለው ማብራሪያ ሲጠይቁ፤ አቶ ዳውድ ስለ ስብሰባው ምንም መረጃ እንዳልደረሳቸው የገለጹላቸው መሆኑንም ይፋ አድርገዋል።
SHARE
Previous article
Next article

LEAVE A REPLY