ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የአረፋ በዓልን ሰብኣዊ ተግባር በመፈጸም እንዲያከብር ሐጂ ሙፍቲ እንድሪስ አሳሰቡ

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የአረፋ በዓልን ሰብኣዊ ተግባር በመፈጸም እንዲያከብር ሐጂ ሙፍቲ እንድሪስ አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የዒድ አል አድሀ አረፋ በዓልን ሲያከብር፤ በእምነቱ የተቀመጡ የወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ክልከላዎችን ተግባራዊ በማድረግ መሆን አለበት ተባለ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እንድሪስ በዓሉን አስመልክቶ ዛሬ መንፈሳዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
 ሙስሊሙ ማኅበረሰብም ይሁን ሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች ኮሮናን በመከላከል ረገድ ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም  ምክር ለግሰዋል።
የዘንድሮውን የአረፋ በዓል የምናከብረው እንደ ቀደሙት ዓመታት በአንድ ላይ ተሰባስበን ሳይሆን ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በመከወን መሆን ይገባዋልም ያሉት ሐጂ ሙፍቲ እንድሪስ፤ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በአረፋ በዓል ላይ የተቸገሩትን በመርዳትና የታመሙትን በመጠየቅ ሰብአዊ ተግባር እንዲፈጽምም ጠይቀዋል።
ሰብኣዊነትን በተግባር በማሳየት እና ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በያለበት ቦታ ሁሉ የዱዓ ጸሎት በማድረግ በዓሉን እንዲያከብር መልዕክት ያስተላለፉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እንድሪስ፤ ከነገ ወዲያ (የፊታችን አርብ)  ለመላው ሙስሊም ማኅበረሰብ እንኳን ለ1 ሺኀ 441ኛው የዒድ አል አድሃ አረፋ በዓል እንኳን አደረሳችሁም ብለዋል።

LEAVE A REPLY