62 ሺኅ ተመልካቾች የሚይዘው የአደይ አበባ ስታዲየም የጣራና የማጠቃለያ ግንባታ ዛሬ ተጀመረ

62 ሺኅ ተመልካቾች የሚይዘው የአደይ አበባ ስታዲየም የጣራና የማጠቃለያ ግንባታ ዛሬ ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ 24 ተብሎ በሚጠራው(መገናኛ)  አካባቢ የሚገኘው የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም የጣራ እና የማጠቃለያ ግንባታ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

ስፖርት ኮሚሽን እንደ ገለጸው ከሆነ ስታዲየሙ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ጠቁሞ፤ ስታዲየሙ በተያዘለት ጊዜ እና ፍጥነት እንዲሁም በተቀመጠው የግንባታ ጥራት መሠረት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
62 ሺኅ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም ያለው አደይ አበባ ስታዲየም  ዘመናዊ ቴክኖሎጂን አሟልቶ፣ የኦሎምፒክና የዓለም ዋንጫ ውድድሮችን ማስተናገድ በሚችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነም ተነግሮለታል።
በገንዘብ ከ5 ነጥብ 57 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚፈጅ የሚጠበቀው የ2ኛው ምዕራፍ ግንባታ፤ በቀጣዮቹጨ 900 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ያለው ኮሚሽኑ፤ አጠቃላይ የግንባታ ወጪው ከ8 ቢሊየን ብር በላይ እንደሆነ ታውቋል።
በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ከ12 በላይ ስታዲየሞች በዚህ ወቅት በመገንባት ላይ እንደሆኑና የተወሰኑት ስታዲየሞች ኢንተርናሽናል ውድድሮችን ማከናወን የሚያስችሉ፣ ዓለም ዐቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆናቸውን ከስፖርት ኮሚሸን መግለጫ መረዳት ችለናል።

LEAVE A REPLY