ትራምፕ ቲክ ቶክ በአሜሪካ ጥቅም እንዳይሰጥ እዘጋዋለሁ አሉ

ትራምፕ ቲክ ቶክ በአሜሪካ ጥቅም እንዳይሰጥ እዘጋዋለሁ አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከቻይና  መጥቶ ዓለምን ጉድ እያስደመመ ያለው “ቲክቶክ” የተባለው ማኅበራዊ ሚዲያ አሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል እንደሚያግዱት  ዶናልድ ትራምፕ ገለጹ።

”እስከ ቅዳሜ ድረስ ባለው ጊዜ ውሳኔውን ማስተላለፍ እችላለሁ” ያሉት አነጋጋሪው ፕሬዝዳንት፤ “ባይትዳንስ” በሚባል የቻይና ድርጅት የሚተዳደረው ቲክቶክ፤ የአሜሪካውያንን ግላዊ መረጃ ለመበርበር ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ሲሉ የአሜሪካ የደህንንት ሓላፊዎች አስቀድመው ጥርጣሬያቸውን እንደገለጹም አስታውሰዋል።
ከቻይና መንግሥት ጋር መረጃ ይለዋወጣል መባሉን ቲክ ቶክ ቢያስተባብልም ፕሬዝዳንት ትራምፕን ጨምሮ በሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም።
አሁን ላይ በመላው ዓለም በሚባል መልኩ  ተወዳጅነቱ እየጨመረ የመጣው ቲክቶክ ፤በአሜሪካ ብቻ እስከ 80 ሚሊየን የሚደርሱ ተጠቃሚዎች ያሉት ከመሆኑ አኳያ እገዳው ለድርጅቱ ከባድ ኪሳራ ሊሆን እንደሚሆን ታምኖበታል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰዐታት በፊት ”ቲክቶክን በተመለከተ፤ አሜሪካ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እናግዳቸዋለን” ሲሉ ተደምጠዋል።
ጉዳዮን አስመልክቶ ከዋሽንግተን ፖስት ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት የቲክቶክ ቃል አቀባይ ሂላሪ ማክኩዌድ ፤ በውሳኔው ላይ አስተያየት ከመስጠት የተቆጠቡ ቢሆንም ድርጅቱ ግን አሁንም ቢሆን የረዥም ጊዜ የስኬት እቅዱ እንደማይጎዳ ገልጸዋል።
 ትራምፕ  እንዲሁ በደፈናው ከቻይና መንግሥት ጋር ግንኙነት አለው ሲሉ የሚከሱት ቲክቶክ እንደሚዘጉት ተናገሩ እንጂ፤ ለመዝጋት ምን ዓይነት ሥልጣን እንደሚጠቀሙ፣ እገዳው እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን እና ምን ዓይነት የሕግ መሰናክሎች እንደሚጠብቃቸው በዝርዝር አላብራሩም። ከገለልተኛ ወገንም እስካሁን በጉዳዮ ላይ ምንም የተባለ ነገር የለም።
ግዙፉ የሶፍት ዌር አምራች ማይክሮ ሶፍት ፤ በቅርቡ ቲክ ቶክን ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው ለባለቤቱ ባይትዳንስ አሳውቆ የነበረ ቢሆንም የፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር ምን ዓይነት ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል እስካሁን ግልጽ አይደለም።
ቲክቶክን በተመለከተ ፕሬዝዳንቱ ያሰተላላፉት መልእክት በአሜሪካና  በቻይና መካካል እየተካረረ የመጣው አለመግባባት ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች እየተነገረ ይገኛል።
የዋሽንግተን ባለሥልጣናትና ፖለቲከኞች ባይትዳንስ በቲክቶክ በኩል የሚሰበስበውን መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል በማለት ሲወነጅሉ፤ ቲክቶክ ሁሉም የአሜሪካ ተጠቃሚዎቹን መረጃ እዛው አሜሪካ ውስጥ እንደሚያስቀምጥና መጠባበቂያው ደግሞ ሲንጋፖር እንደሆነ በምላሹ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY