ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ትላንት ኦገስት 1 ቀን በቫንኮቨር እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኦሮሚያ ክልል በጽንፈኞች ጥቃት የደረሰባቸውን ወገኖች በመደገፍና ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑትን አካላት በማውገዝ ነው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡት።
ሰልፈኞቹ የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን ዘግናኝ ግድያ፣ ጭፍጨፋና የንብረት ውድመት እንዲቆም እንዲሁም የድርጊቱ ፈጻሚዎች እንዲጠየቁ አሳስበዋል።
የካናዳ ፓርላማ ተመራጭ የሆኑትና ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከእስር እንድትፈታ የካናዳ መንግስት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ በማሳደር የሚታወቁት ሜምበር ኦፍ ፖርላሜንት ፒተር ጁሊያኒ እና የአካባቢው ተመረጨ ሚስተር ራጅ ቻዋን በስፍራው ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
ፒተር ጁሊያኒ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ዘርና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ በትኩረት እንደሚከታተሉ ገልጸው ድርጊቱን አውግዘዋል። ያለአግባብ የታሰሩ ንጹሀን የተቃዋሚ መሪዎች እንዲፈቱም ጠይቀዋል።
ባለስልጣናቱ የካናዳ መንግስት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ከኢትዮጵያውያኑ ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ ከያዟቸው መፈክሮችም
- የዘር እና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ እንቃወማለን
- ንጹሀንን መግደል ይቁም
- ልዩነቶችን ኣንድነታችን ነው
- እስክንድር ነጋ ይፈታ
- መንግስት የኢትዮጵያን ጥቅምና ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል የሞከሩትን ሀይሎች ለፍርድ ያቅርብ። የሚሉ ይገኙበታል