የኮንዶሚኒየም ግንባታ በቅርቡ 125 ሺኅ ቤቶች ለእጣ ሊያቀርብ ነው

የኮንዶሚኒየም ግንባታ በቅርቡ 125 ሺኅ ቤቶች ለእጣ ሊያቀርብ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ብዙ የተባለለትና በርካታ ተመዝጋቢዎች ተስፋ የቆረጡበት የኮንዶሚኒየም ግንባታ ከእደላና የቤት ባለቤትነት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለበት በሚነገርበት በዚህ ወቅት ብዛት ያላቸው ኮንዶሚኒየሞች እየተገነቡ ነው ተባለ።

በአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው ከተሾሙ በኋላ ግልፅ የሆነ የተረኝነትና የዘረኝነት መዋቅር በመንግሥታዊ መዋቅሮች ከላይ እስከ ታች የዘረጉት ታከለ ኡማ  ከተማ  አስተዳደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማቅረብ 125 ሺኅ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየገነባ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የመስተዳደሩ ምክር ቤት ሠባተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ እያካሄደ ባለበት ወቅት ምክትል ከንቲባው የ2012 በጀት አፈፃፀም ሪፖርት ሲያቀርቡ፤
 ውዝፍ የባንክ ቤት እና የወሰን አከላል ሂደቶች ችግር ቢፈጥሩም  የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዜጎች ለማቅረብ በትኩረት እየሠራን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ቤቶቹ በትክክል ለተመዝጋቢው መሰጠታቸው ከወዲሁ አጠራጣሪ ቢሆንም በግንባታ ላይ ከሚገኙ የጋራ መኖርያ ቤቶች መካከል 95 ሺኅ የሚሆኑት የ20/80 ቤቶች እንደሆኑና 29 ሺኅ ቤቶች ደግሞ በ40/60 መርሀ ግብር ግንባታቸው እየተፋጠነ መሆኑ ታውቋል።
ከንቲባ ታከለ ባለፉት ሁለት ዓመታት የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ሥራዎች በመንግሥት በኩል መከናወናቸውን በሪፖርታቸው ቢገልጹም፤  ለመምህራንና ለፓርቲ አባላት በሚል በየካ አባዱ፣ ገላን፣ ኩዬ ፈጬና ቦሌ ሐራምሳ አካባቢ ጥቂት የማይባሉ የጋራ ቤቶች ብሔር ተለይቶ እንዲታደሉ መደረጉ አይዘነጋም።
በቅርቡም በተመሳሳይ መልኩ በተለያየ መንገድ ርክክብ ሳይደረግባቸው የቆዮ ነባርና ግንባታቸው ያለቀ አዳዲስ ኮንዶሚኒየሞች መሀል የተወሰኑት ለተረኞች ውስጥ ለውስጥ መተላለፍ መጀመሩን ተከትሎ መረጃዎች ሾልከው በመውጣታቸውና ከብዙኃን ማኅበረሰብ ዘንድ በመድረሱ እደላውን ለማቋረጥና ከንቲባውም መረጃውን ለማስተባበል መዘጋጀታቸው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY