ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚያደርጉትና ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ዛሬ መቀጠሉ ታወቀ።
በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ለ11 ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ከሁለት ሳምንታት በፊት የተቋረጠው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፤ የሦስትዮሽ ድርድር ከሳምንት በፊት ሊቀጥል ታስቦ የነበረ ቢሆንም ሱዳን ለአንድ ሳምንት ይዘግይልኝ ስትል ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት ወደ ዛሬ ተሸጋግሯል።
ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ለቀጣይ አንድ ሳምንት እንደሚቀጥል የተነገረው ይህ የሦስትዮሽ ድርድር፤ ቀደም ሲል ከተካሄደው የ11 ቀናቱ ድርድር በኋላ ለመሪዎች በቀረበው ሰነድ መሠረት መሪዎቹ ባስቀመጡት አቅጣጫ የሚቀጥል ነው ተብሎለታል።
ይህ ዜና እሰከተጠናቀረበት ሰዐት ድረስ ሀገራቱ እያካሄዱት ባለው ድርድር የተገኘ አዲስ ውጤትም ሆነ ልዮነት በመንግሥት በኩል የወጣ ይፋዊ መግለጫ የለም።