ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከውጭ የሚገቡ ተጓዦች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ አለባቸው ቢባልም በኢትዮጵያ ይህን ለማድረግ አስቸጋራ ሁኔታዎች አሉ ተባለ።
በሀገሪቱ ይህንን ምርመራ በማድረግ ውጤት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል የሆነውና አብዛኞቹ የውጭ አገር ተጓዦችን የሚያስተናግደው ተቋም የምርመራ ፈላጊዎች ቁጥርና አገልግሎቱ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ተገልጋዮች ገልጸዋል።
የአየር በረራ አገልግሎት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ በመቆየቱ ለወራት ሲጠባበቁ የነበሩ ተጓዦች ይህንን ምርመራ ለማድረግ ከባድ ፈተና እንደሆነባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ለዚህ ምክንያት የቀረበው ምርመራውን የሚያከናውነው ተቋም የወሰደውን ናሙና ውጤት ለማሳወቅ ቢያንስ 48 ሰዐታትን መውሰዱ ነው። ይህ አሠራር እንደየሀገሩ የሚለያይ በመሆኑ እሰከ 96 ሰዐት የሚቆይባቸው ሀገራትም መኖራቸው ታውቋል።