አሜሪካ ለጽኑ ታማሚዎች የሚውሉ 250 ሜካኒካል ቬንቲሌተሮችን ለኢትዮጵያ ሰጠች

አሜሪካ ለጽኑ ታማሚዎች የሚውሉ 250 ሜካኒካል ቬንቲሌተሮችን ለኢትዮጵያ ሰጠች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ ከመንሰራፋቱ ባሻገር፣ የሟቾች ቁጥር መጨመሩን ቸከትሎ አሜሪካ ለኢትዮጵያ 250 ሜካኒካል ቪንቲሌተሮች መስጠቷ ታወቀ።

ድጋፉን ያስረከቡት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምሳደር ማይክል ራይነር ሲሆኑ፥ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተረክበዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ማይክል ራይነር አማካይነት ለኢትዮጵያ የቸበረከተው ሜካኒካል ቬንቲሌተር፣ በኮቪድ-19 ቫይረስ በጽኑ ለታመሙ ሰዎች የአየር ሥርዓት ፍሰትን ለማስተካከል (የመተንፈስ አቅምን ለማጎልበት)  የሚረዳ ነው ተብሏል።
 የቫይረሱ ወረርሽኝ መከሰትና መስፋፋቱን ተከትሎ በዓለም ላይ እጅግ ተፈላጊና ውድ መሳሪያ መሆኑ የተነገረለትና ከአሜሪካ በእርዳታ የተሰጠው የሜካኒካል ቬንቲለተር የአንዱ ዋጋ 8 ሺኅ የአሜሪካ ዶላር ሲሆን፤ በድምሩ 70 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር እንደሚያወጣ ተነግሯል።
የአሜሪካ መንግሥት  250 ተጨማሪ ሜካኒካል ቪንቲሌተሮችን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ በሂደት ላይ መሆኑን እና አሁን ሀገር ቤት የገቡት የመተንፈሻ መሳሪያዎችን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ድርጅት ወደ ክልሎች የሚያሰከፋፍል መሆኑን ከደረሰን ዜና መረዳት ችለናል።

LEAVE A REPLY