የሊባኖስ ነዋሪዎች ለደረሰው አደጋ ተጠያቂው መንግሥት ነው ሲሉ ቁጣቸውን አሰሙ

የሊባኖስ ነዋሪዎች ለደረሰው አደጋ ተጠያቂው መንግሥት ነው ሲሉ ቁጣቸውን አሰሙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  ማክሰኞ እለት የደረሰው ከባድ ፍንዳታ በቸልተኝነት ምከንያት የተፈጠረ ነው ሲሉ የቤይሩት ነዋሪዎች ቁጣቸውን መንግሥት ላይ ገለፁ።

ፕሬዝደንት ማይክል ኦውን ፍንዳታው ባገጠመበት ቦታ ላይ 2ሺኅ 750 ቶን የሚመዝን አልሙኒየም ናይትሬት ደኅንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለሥድሥት ዓመታት ተከማችቶ ነበር ሲሉ መግለጻቸው የቁጣው መንስዔ ሆኗል።
በሊባኖሷ መዲና ቤይሩት በተከሰተው ከባድ ፍንዳታ ቢያንስ 135 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ4 ሺኅ በላይ ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸው መረጃዎች ያሳያሉ።
በሊባኖስ የፀጥታ ኃይሎች ፍንዳታው የደረሰበትን ስፍራ አጥረው የነፍስ አድን ሠራተኞች በፍርስራሽ ውስጥ ተቀብረው ያሉ አስከሬኖችን እየፈለጉ ቢሆንም አሁንም በርካቶች መጥፋታቸው በመነገር ላይ ነው።
በፍንዳታው የተጎዱ እና የህክምና ድጋፍ የሚፈልጉ ዜጎችን ለማከም የሊባኖስ ሆስፒታሎች የአልጋ እና ህክምና ቁሳቁስ እጥረት እንዳለበት የጤና ሚኒስትሩ ሃማድ ሃሰን የገለጹ ቢሆንም ነዋሪዎች ግን ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው መንግሥት ነው እያሉ ናቸው።
ከአደጋው በኋላ ረቡዕ ዕለት መንግሥት የቤይሩት ወደብ ባለሥልጣናት ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ምርመራ በመጀመሩ በቁም እስር ውስጥ ሲሆኑ፤ የሊባኖስ የጦር ሓላፊ ለፍንዳታው ተጠያቂ ሆነው የሚገኙት ላይ ከፍተኛ ቅጣት ይተላለፍባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY