የአውቶሜሽን መተግበሪያ እና የኦንላይን ትምህርት የዲጂታል መረጃ አስተዳዳር ሥርዓት ይፋ ሆነ

የአውቶሜሽን መተግበሪያ እና የኦንላይን ትምህርት የዲጂታል መረጃ አስተዳዳር ሥርዓት ይፋ ሆነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጄንሲ ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባባበር ያዘጋጁት የአውቶሜሽን መተግበሪ እና የኦንላይን ትምህርት መማሪያ የዲጂታል መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ተመረቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዷለም አድማሴ አንድ ዓመት የፈጀው ፕሮጀክት በስኬት እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማሪያም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የአሠራር ሥርዓትን በኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጀ የማዘመን ሥራ በሠፊው እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
የተመረቀው የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት የእውቅና አሰጣጥ ሥራን ለማዘመን እና የመረጃ አያያዝ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚያግዝም አረጋግጠዋል።
የመረጃ አስተዳዳር ሥርዓቱ በሀገራችን የዲጂታል ሊትሬሲ ትግበራን ለማስፋፋት የተጀመረውን ጥረት የሚያጠናክር ነው ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በቴክኖሎጂ የመደገፉ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።
 የፕሮጀክቱ መሪ እንዲሁም የቀድሞ የቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ኢኒስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር  የነበሩት አቶ ሳንዱካን ደበበ ፤ ሥራው ሲጀመር ከሌሎች ተቋማት ጋር እንደሚደርገው የትብብር ሥራ ብቻ ሳይሆን በትምህርቱ ዘርፍ ላይ ትልቅ መሠረት ለመጣል ታስቦፕ መሆኑን ከመጠቆማቸው ባሻገር፤  የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰጣቸው ፈቃድ መሠረት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ቁጥጥር ለማድረግ፣ የእውቅና ጥያቄዎቸን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስጠት፣ በእያንዳንዱ ተቋም የተመዘገቡ ተማሪዎችን ከመቆጣጠር ጀምሮ ለተለያዩ የትምህርት ተቋማት የጥራት አገልግሎቶችን በተገቢው ሁኔታ እንዲተገብሩ  የሚደግፍ መሆኑን አብራርተዋል።

LEAVE A REPLY