በሞቃዲሾ ዛሬ በደረሰ ፍንዳታ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች ላይ ጉዳት የመቁሰል...

በሞቃዲሾ ዛሬ በደረሰ ፍንዳታ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች ላይ ጉዳት የመቁሰል አደጋ ደረሰ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሶማሊያ ዋና መዲና ሞቃዲሾ የጦር ካምፕ አቅራቢያ ዛሬ በደረሰ ፍንዳታ 8 ሰዎችን መገደላቸውን እና 14 ሰዎች ላይ ጉደት መድረሱ ታወቀ።

ጉዳዮን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የሶማሌ ጦር ሓላፊ ኮሎኑል አህመድ ሙሴ ፍንዳታው ያጋጠመው በቅርቡ የተከፈተ ስታዲየም አቅራቢያ በሚገኘው የሶማሊያ ጦር 12ኛ ብርጌድ መሆኑን ለአሶሼቲድ ፕሬስ ተናግረዋል።
ዛሬ በሞቃዲሹ ላጋጠመው ፍንዳታ ምክንያት ምን እንደሆነ  እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን የዓይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት ስታዲየሙ አቅራቢያ በሚገኘው የጦር ካምፕ አቅራቢያ መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ጥቃቱን እንዳዳረሰ ተገምቷል።
“ዳለሳን” የተባለው ራዲዮ የፍንዳታው ድምጽ ከየትኛውም የከፍል ይሰማ ነበር በማለት የአደጋውን ጥልቅነት የዘገበ ሲሆን፤ የዓይን እማኞች በበኩላቸው  ፍንዳታው ካጋጠመ በኋላእዠ የሶማሊያ ወታደሮች ተኩስ ከፍተው እንደነበር ለሮይተርስ አስረድተዋል።
ሱማሊያን መናኸሪያው  ያደረገው ጽንፈኛው ቡድን አልሸባብ  ቀደም ሲል የጦር ካምፖችን እና የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን ሲሰነዝር መቆየቱ ይታወቃል።
ይህን ተከትሎ ለጥቃቱ አልሻባብን ተጠያቂ ያደረጉ በርካቶች ናቸው።በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወደ አንድ የገበያ ማዕከል ሊገባ የሞከረን አጥፍቶ ጠፊ ለማስቆም የሞከሩ ሁለት ጥበቆች፤ አጥፍቶ ጠፊው እራሱን አጥፍቶ ጠበቆቹን መግደሉ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY