ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ በተለይም የኦሎምፒክ ስፖርት እንቅስቃሴ ላደረጉት የላቀ አስተዋጽዖ ሽልማት ሊበረከትላቸው ነው።
ወጣቱ የኢትዮጵያ መሪ ለኦሎምፒክ ስፖርት ዕድገት ከፍተኛ ድጋፍና አስተዋጽኦ ላደረጉ መሪዎች እና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች የሚሰጠውን ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን ይፋ ያደረገው የአፍሪካ ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) ነው።
ማኅበሩ የኦሎምፒክ ስፖርት እንቅስቃሴና አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ ንቅናቄ በማድረግ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአፍሪካ የስፖርቱን ዘርፍ ትልቁን ሽልማት መቀዳጀት ችለዋል ሲል አሞካሽቷቸዋል።
የስፖርት ማኅበሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሽልማት በደማቅ ሥነ ሥርዓት በቀጣይ በሚመረጥ ቦታና ጊዜ እንደሚያበረክትም ተናግሯል።
መቀመጫውን በናይጄሪያዋ አቡጃ ከተማ ያደረገው የአፍሪካ ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር ሰኔ 28 ቀን 1981 የተቋቋመ ሲሆን

























