በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ሥርጭት ቁጥር በ20 ሺኅ ከፍ ማለቱ ተረጋገጠ

በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ሥርጭት ቁጥር በ20 ሺኅ ከፍ ማለቱ ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኤች አይ ቪ ቫይረስ ካለፈው ዓመት ሲነፃፀር በሀገር ዐቀፍ ደረጃ  በሀያ ሺኅ (20,000) ከፍ በማለት የመስፋፋት ደረጃውን እንዳሳደገ ታወቀ።

በ2011 ዓ.ም ከነበረው በቫይረሱ ከተያዙ 649 ሺኅ ወደ 669 ሺኅ ሰዎች ማደጉን ተከትሎ ቫይረሱ ሀገሪቱ መስፋፋት በላቀ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን ያሳያል ተብሎለታል።
የፌደራል ኤች አይ ቪ/ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ለስርጭቱ መጨመር ምክንያት በህብረተሰቡ ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ትኩረቱን መቀነሱ እንደሆነ ጠቁሟል።
ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ የኮቪድ 19 ቫይረስ በመከሰቱ የምርመራ ሥራዎች መቀዛቀዝ ሌላው ምክንያት እንደሆነም ጽ/ቤቱ አረጋግጧል።
የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶክተር ዳንኤል በትረ የቫይረሱ ሥርጭት በሶማሌ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ብሔረሰቦች ክልል ውጭ በሚገኙ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በአሁኑ ወቅት በወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቅተዋል ብለዋል።
ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ከተስፋፋባቸው ጋምቤላ 4 ነጥብ ስምንት በመቶ በመሆን ቀዳሚውን ሥፍራ ሲይዝ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬደዋ አስተዳደር፣ ሀረር፣ አፋር፣ ትግራይ፣ አማራና ቤኒሻንጉል ጉምዝ በቅደም ተከተል ቫይረሱ በያዝነው ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ የተንሰራፋባቸው ሆነዋል።

LEAVE A REPLY