ከሀዲው ወያኔ ሃገርና ህዝብ ሊመራ አይችልም || ገብረመድህን አርአያ (አውስትራሊያ-ፐርዝ)

ከሀዲው ወያኔ ሃገርና ህዝብ ሊመራ አይችልም || ገብረመድህን አርአያ (አውስትራሊያ-ፐርዝ)

 ነሃሴ 2/2012

ከሃዲና ባንዳ የማፍያ ስብስብ ህወሃት (ወያኔ) ሃገርና ህዝብ ሊመራ አይችልም፤ በህዝብም ተቀባይነት የለዉም!!!

*ህ ወ ሃ ት ካለ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ሉአላዊነት የለም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላምና በአንድነት በአብሮነት በእፎይታ መኖር አይችልም፣ የትግራይ ህዝብም ከባርነት ስርአትና ጭቆና አይላቀቅም፣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ህዝብ ለመበተን ሃገር አልባ እንዲሆን በክፉ ጥላቻ የተዋቀረ ድርጅት ወያኔ ነው*!!

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!! ሃገርና ህዝብን ማዳን የሁሉ ኢትዮጵያዊ ተግባርና ሃላፊነት ግዴታም ጭምር ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያ ባንተ በልጆችዋ ተከብራና ታፍራ በውጭ ጠላት ለዘመት ሳትደፈር የመጣች ባለ አኩሪ ታሪክ ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት ብለን ለመናገር ድፍረትና በቂ ሞራልም አለን። ምንም እንኳ የተለያዩ ወራሪና ቅኝ ገዢ ቢሞኩሩም በልጆችዋ ሀይልና ጀግንነት ኢትዮጵያ በጠላት እጅ ሳትወድቅ ጠላትም ተደጋጋሚ ጥቃቶች ቢሰነዝርም ጀግናው ኢትዮጵያዊው ሃገሬ ኢትዮጵያ በውራሪ ጠላት አትደፈርም ብሎ በሚያስኮራ የጀግነት ሙያ ጥበብና ብልሃቱ ጠላትን በማሸነፍና በማሳፈር ድል በድል. በመጎናፀፍ ጠላትን አሸንፎ የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና ታሪክዋን የህዝብዋን አንድነት አስከከብሮ ለሺህ ዘመናትን ደሙን አፍሦሶ አጥንቱ ከስክሶ እንደ አንበሳ እያገሳ ኢትዮጵያ በማንም ወራሪ ጠላት ሳትደፈር እድሜ ልጆችዋ ታፍራ ተከብራ የመጣች ባለታሪክ ሃገር ይህች ኢትዮጵያ ብቻ ናት።

ዛሬ ግን በጉያዋ የተፈጠረ ትግራይን እወክላለ ትግራይ ከአማራ ቅኝ አገዛዝ አውጥቸ ሃርነትዋ ታገኝለች የሚለው ሃገር አፍራሽ የህዝብ አንድነት አውዳሚ ሽብርተኛው ወያኔ ኢትዮጵያና ህዝብዋ ለብዙ ችግርና መከራ የዳረጋት በባእዳን የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጠላቶች የተፈጥረ MERCENARY የማፍያ ስብስብ ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ነው፤ ወያኔ ገና ሲፈጠርም ባንዳና የባንዳ ልጅች ተሰባስበው የፈጠሩት እንዲፈጠርም ከመነሻው ትልቅ የሞራል ድጋፍና በገንዘብም በሃሳብም ጭምር እየተባበሩ ለዚህ ደረጃ ያደረሱት ሊብያ፤ሱዳን፤ግብፅ በግንባር ቀደምት የሚጠቀሱ ናቸው።

ይህ ድርጅት ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በሆኑ ሃሎች ተፈጥሮ ሲያድግ የሚከተለው አላማ ጸረ ኢትዮጵያ ሏአላዊነት ጸረ ኢትዮጵያ እንድነት ሆኖ የተፈጠው፤ በዚህም መሰረተ እቅዱ ከመጀመሪያ መነሻው ተሰልፎ የመጣ ኢትዮጵያ መበታተን አንድነትዋን ማፍረስ ግዳጅ አንግቦ ደደቢት በረሃ በየካቲት ወር 1967 ኣም የወረደው፤ይህ የባእዳን ቅጥረኛ ወራሪ ጠላት ሃገር ፍራሽ እንጂ ወያኔ ኢትዮጵያዊ ወይም ኢትዮጵያዊ ስሜት የሌለ መሆኑ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ቀደም ብሎ ያረጋገጠ ሃቅ ነው። ሃገርና ህዝብ የሚበታትን የሚያፈርስ የውጭ ወራሪ ጠላት ባእድ ብቻ ነው፤ እንደ ህወሓት የባእዳን ቅጥረኛ (MERCENARY) የኢትዮጵያ አንድነት በማፍረስ የህዝብዋ አንድነት በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ሃገር በታኝ (ወያኔ) ህ.ወ.ሓ.ት የመሰለ በታሪክም አልታየም የለምም፡፡

ለዝሁም ተግባሩም ብዙ እውነታዊ ማስረጃ ማቅረብ ማስረጃዎች አሉ፤በግላጭ ማቅረብ ይቻላል!ብዙ ክህደትና ወንጀል የሰራ ወንጀል አድራጊ ህ ወ ሃ ት ነው፡፡ለማስታወስ ያህል አንድ የካዲ ማንነቱን ሃቅ እውነታ ላቅርብ እፈልጋለሁ ይሕም በተግባር የሰራው አሳፋሪ የሃገር ክህደት ነው፤ የሱማሊያው(መቃድሽ)መንግሥት በሰይድ ባረ የሚመራ መንግሥት ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት በ1969 ዓም ከዚሁ ወራሪ መንግሥት በግንባር ቀደምትነት ከጎኑ ቆሞ የተሰለፈው ህወሓት ነው፤ ወያኔ ከትግራይ ተንስቶ ኢትዮጵያ ኦጋዴን ግዛት ድረስ ተጉዞ በታጋይ ስየ አብርሃ የሚምሩ 3 የህ.ወ.ሓ.ት.ሃይሎች ይዞ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት የሚወጉና የሚገድሉ ከህ ወ ሃ ት ታጋዮች በማሰለፍ ይዞ መሄዱ የትናንት የህወሃትድርጊት ነው፤ ከወራሪው የሱማሊያው መንግሥት ጎን ተሰልፎ የኢትዮጵያን ሠራዊት የወጋ ያደማ ህወሓት ነው፡፡ የጠላት ጠላት አረሜን ከሃዲ ፀረ ሃገርና ፀረ ህዝብ፤ ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለመበታተን ያልጀመረውና ያልጎነጎነው እቅድ አልነበረውም።

በመቃድሾ ሱማልያ መንግሥት በኩል ህ ወ ሃ ት ላደረገው መልካም ትብብር ተብሎ በ1970 ኣም ማለቅያ አካባቢ ለዚህ ወለታና ካሣ ተብሎም የሰይድ ባሬ የሱማሊያ መንግሥት 1. በወቅቱ የስም መጠሪያው/ ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ /ተ.ሓ.ህ.ት/.(የዛሬዋ ህ.ወ.ሓ.ት)አመራሮች ለሁሉ በስም ዝርዝራቸው ሕጋዊ በሆነ ስርአት ተዘጋጅቶ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቲክ ፓስ ፖርት ገንዝብም ጭምር ለዓመታት የተጠቀሙበት ተላከላቸው 2. በአነስተኛ መርከብ ተጭኖ በየዓይነቱ ነብስ ወከፍ መሳርያ ከነ ጥይቱ ካላሽን ኮፍ፤ ሲሞኖቭ ሰሚ አውቶማቲክ ባልመነፅር ራሻ ሰራሽ ፤ የእጅ ቦምብ አሜሪካና ቻይና ሰራሽ ወ.ዘ.ተ፣ ወደ ሻእብያ ተልኮ በሻእብያ በኩል ደረሳቸው በትክክልም ትግራይ በረሃ ገባ የወያኔ አመራሩም በፈንጠዝያና በእልልታ ተቀብለዋል፤ ለዚሁም ዋናው ምስክር አሁን በሥልጣን ያሉ የኢርትራ መንግሥት መሪዎች እውነታውን ለማረጋገጥ በቂ የእማኝ ምስክር ናቸው።

ይህ ከሆነ በኋላ በ1972 ኣም መጀመሪያ አራት(4) የህወሃት አመራር ግብዕ (ኢጅብት) ተልከው ከአንድ ወር ቆይታ በኋላ ተመለሱ የሄዱም 1 ግደይ ዘርአጵዮን በመሪነት፤2 ስየ አብርሃ 3 አባይ ጵሃየ 4 ዘርአይ አስገዶም ነበሩ፡፡ለምን እንደሄዱ ሚስጥሩ የአመራሩ ጉዳይ ነው፡፡ 2ኛ በ1975 ለሱዳን ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የሃገር ዳር ድንበር ለሱዳን መንግሥት አሳልፈው በማን አለብኝ የሞተ ብጣሽ ወረቀት የ1902ዓ.ም.ሱዳን ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት፤ የአንድ ሃገር ሏላዊነት ክብርና ሕግ በመፃረር ከጎንደር ጠቅላይ ግዛት በድርድር ለስዳን መንግሥት የሽጠው ሰፊው ለም መሬት አሁን በሰላማዊው የጎንደር ህዝብ ከባድ ችግር ፈጥሮበት ያለው ህ.ወ.ሓ፣ት.ያመጣው ማለቂያ የለሌው ችግር ነው።

የህ.ወ.ሓ.ት ማፍያ ጉጅሌ አመራር በኢትዮጵያ የፈፀመው ክህደትና ወንጀል ብዙ ነው፤ የዘር ማፋት ወንጀል በአሰቃቂ በአሬመናዊ መልኩ በአማራው ህዝብ ፈፅመዋል፤ ወያኔ በ1967 ዓ/ ም የካቲት ደደቢት እንደወረደ በትግራይ ህዝብ ላይ ቀስ በቀስ የባርነት አመራሩ በመዘርጋት በ1968 ዓ.ም የካቲት ወር አንስቶ የትግራይ የቤተ ክህነት ሊቃውንት ከየገዳማቱ፤ አርበኞች፤ በህዝብ የተከበሩ ታላላቅ ስዎች፤የታሪክ ሊቃውንት፤ በአፈና ከየቤታቸው ከእርሻ መሬታቸው ከየቦታው በአፋኝ ታጋዮች እየተያዙ ፀረ ትግራዋይ ከሃዲ የሸዋ አማራ አሽከር እየተባሉብ የተለየ የውሽት ስም እየስጡ በጥይት እየተደብደቡ ተገድለው ያለቁት ቤቱ ይቁጥረው፤ በወረዳ በገጠር የሚኖሩ ከዚሁ የሽብር ጥቃት ለመሸሽ ለማምለጥም

ብሎ ያለውን እየጣለ የሸሸ ወጣት ሽማግሌ እናቶች ልጆች ቤቱ የፈረሰው በህ ወ ሃ ት ነው፤ ህዝቡም ጨረሱት ለችግርና ስቃይ ዳረጉት በ1968 ዓ.ም. አጋማሽ የተጀመረው የትግራይ ህዝብ ማጥፋት ከዚሁም ተያይዞ ከ1970ዓ.ም. አንስቶ ነብስ አጥፊ(ፈዳያን ) TERRORIST በድርጅቱ ም/ሊቀ መንበር ታጋይ ግደይ ዘርአፅዮን የሚመራ ሽብርተኛና ነብስ አጥፊ ገዳይ ቡድን አጠናክረው በማቋቋም በትግራይ ከተሞች ዓድዋ፤ ሽሬ፤ አክሱም፤ ተምቤን፤ ዓዲግራት፤ መቀሌ፤ ሁለት አውላዓሎ (ውቅሮ) ማይጨው በቡድን በቡድን እየተከፋፈሉ ተመሳስለው በመግባት ተማሪው፤ አስተማሪ፤ የመንግሥት ሠራተኛው፤ የየከተማው ነዋሪዎች ታላላቅ ሰዎች በጠራራ ፀሓይ በተለያቱ ቀንና ሳአት በመግባት ህዝቡን ፈጁት፤ ወያኔ በትግራይ የሁለት ትውልድ ዘር ያጠፋው የገደለ ወንጀለኛ የሽብር መሪ ትግራዋይ ሳይሆን ትግራይን ለማጥፋት የተፈጠረ ሽብርተኛ ዘረኛ የሌቦች ስብስብ ማእከል መሆኑም የትግራይ ሁሉ ያውቃል። በ1977 ዓ.ም.በወረደው ሂወት ቀዛፊ ድርቅ በጊዜው ትግራይ በዚሁ ሃለኛ ድርቅ በተመታች ሞላው የትግራይ ህዝብ በቆመብት በሄደብት እንድቅጠል እየረገፍ ሲሞት ሲያልቅ የዓለም ህዝብ ተረባርቦ የትግራይ ህዝብ ሂወት ለማዳን እጅግ መጠነ ሰፊ እርዳታ ከዓለም የጎረፈው እጅግ ትልቅ እርዳታ የህ ወ ሃ ት መሪዎች እነ ስብሃት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ፤ ሥዩም መስፍን፤ አባይ ጵሃየ፤ ወዘተ ለትግራይ ህዝብ ምንም ሳያቀስሙ ሙሉ በሙሉ ሽጠው ወታደራዊ መሣሪያ የገዙበት ለማለሊት<ማርክሰ ለኒናዊ ሊግ ትግራይ> ድርጅ ት ከ36 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ ተምቤን ወሪዒ ላይ ሲያቋቋሙ አንድ ወር ሙሉ ህወሃት በድግስና በስካር ሲንደላቀቅ፤ በማይል ጃክሰን ሙዚቃ ድግስ ሲደንሱ፤ ሲዳር ሲሞሸር ገነቱ ሲያዩ፤
በሌላው ደግሞ የትግራይ ህዝብ ሂወቱን የሚያድንባት መፍትሄና መንገድ ሁሉ በጭለማ ታጥሮበት በረሃብ በበሽታ በሄደበት በተጓዘበት በተደራራቢ ችግር በውሃ ጥም ሲሞት ሲረግፍ ሲያለቀ፤ ቀባሪ ያጣ ትግራዋይ የጅብ ቀልብ ሲሆን፤ወያኔ ህወሃት በስብሃት ነጋና በመለስ ዜናዊ የሚመሩ መሪዎች ቀሪው አመራርም ሁሉ የተረባረቡት በገበያ ነበር ለትግራይ ህዝብ የመጣው መጠነ ሰፊ ነብስ አድን እርዳት በሱዳን፤በሶሪያ፤ሊብያ፤ፎርኦን ኢጅፕት፤ ሊባኖስ ሃገር ወዘተ፤ በበርካታ የአረብ ሃገሮች ገበያ በማውረድ ሽጠው በጮማና በዊስኪ ቢራ ማእበል ተጥለቀለቁ በገንዘብም ከዓለም ሃብታም ቱጃሮች ጎን ተሰለፉ ከድሃ ትግራዋይ በድርቅና በርሃብ በበሽታ የትግራይ እያለቀ በትግራይ ህዝብ ሂወት አድን ሽጥው ቱጃር ሆኑ እጅግ ትልቅ እርዳታ ዘረፉት፤ በትልልቅ ዐለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ተጭኖ ለገበያ ወደ አረብ ሃገሮች አወረዱት እንግዲህ ህወሓት ማለት ይህ ነው፤ ገዳይ፤ ዘራፊ፤ ሌባ፤ ሽብርተኛ፤ በህዝብ ስም የሚነግድ ሸቃጭ ደላላ የማፍያ ቡዱን የትግራይ ህዝብ አረሜኔ ጥላት፤ ተወዳዳሪ የማይገኝለት እጅግ ክፉ የሃገርና የህዝብ ነቀርሳ፡ ሌላ የፈፀሙት አሰቃቂና አሳዛኝ ወንጀል በ1980 ዓም በሰኔ ወር የሓውዜን ህዝብ በደርግ ሚግ 27ና 23 አይሮፕላኖች ሄሊኮፕቶሮች ጭምር በእጅ አዙር ያስደበደቡት የወያኔ መሪዎች ሰላማዊ ለገበያ የወረድ ህዝብን በፈጠሩት ውስጣዊ የመስመር ግኑኝነት በወቅቱ የደርግ ባለስልጣን ሻምበል ለገሠ አስፋው የትግራይ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩ በመለስ ዜናዊ እና በስብሃት ነጋ ሓውዜን በደርግ እጅ በሚግ አሮፕላን እንድትደበደብ ሁለቱ የወያኔ መሪዎች ሃሳቡን በማዘጋጀት በህወሓት ነባር ታጋይና የህወሓት ወታደራዊ ደህንነት ዋና ሃላፊ ሃይሉ በርሄ(ሃይሉ ሳንቲም)ከሻምበል ለገስ አስፋው የሚግናኙበት መንገድ ፈጥረው

ኢንፎርመሽን በመለዋወጥ እቅዳቸው ከፈጸሙ በኋላ ሰኔ ወር 15 ቀን 1980 ዓም ሓውዜን በድርግ ሚግ ተደበደበች ወደመች ከ5000 ህዝብምን ተገደለ አለቀ ከተማዋም ሙሉ በሙሉም ወደመች ህወሓት ወያኔም በመሰሪ ተግባሩ ለራሱ ጥቅምና ዝናተቀባይነት አገኛለሁ ብሎ ኢትዮጵያዊ የሓውዜን ህዝብ አስገደለ አስጨፈጨ ይህን ከባድ ረቂቅ ወንጀል እንዲፈፀም ያደረገው ያስፈፀመው ህወሓት ነው፡፡

ህወሓት በኢትዮጵያና በህዝብዋ ያልሰራው የማይሰራው አሁንም ሤራና ገመና የለም ሃሳቡና አላማው ኢትዮጵያና ህዝብዋም ጭምር በታትኖ ሃገር አልባ ለማድረግ ዋናውና መሰሪ እቅዱ መሆኑ ጭብጥ እንያዝ፤ቢሆንም ግን አንድ የውጭ ባእዳን ቅጥረኝ ወያኔ ባሰበው ሳይሄድ በኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ሃይል ክንድ ተሰባብሮ ወደ መቃብር ህልፈቱ ይገባል፡፡

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!!

ከማንም በላይ አንተ የህወሓት ባህሪና ምንነት ጠንቅቀህ የምታውቅ ታላቅ ህዝብ ነህ። ህወሓት፥ ከፋፋይና ዘረኛ፤ ሌባና ዘራፊ፤ ሽብርተኛና ገዳይ፤ ፀረ ሃገርና ህዝብ፤ የሰው ልጅ ሰብዓዊ መበት ረጋጭ፤ ወ.ዘ.ተ. በሚገባ ታውቀዋለህ፤ ባንዳ የባንዳ ልጆች መስባሰቢያ በሆነው ህ.ወ.ሓ.ት. ተሰባስበው የፈፀሙት የሠሩት ከፍተኛ ወንጀሎች አንተ ታውቀዋለህ ፤በዓይንህ ያየኽው የ27 የሲኦል ሰቆቃ በገዛ ሃገርህ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረህ በችግር በርሃብ በበሽታ የተሰቃይህ አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ በህወሓት በባርነት ሸንሸል ታስረህ 27 ዓመት ሙሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያ በመሆንህ የፋሽሽት
ህወሓት የሲኦልና የመከራ ፋሽሽታዊ አገዛዝ የወረደብህ አንተ ሃገር ወዳድ ሉአላዊት ኢትዮጵያን ያስከበርክ ስለሆንክ ነው በፋሽሽታዊ ወያኔ ግፍ 27 አመት የቁም ስቃይ የተሰቃየኽው፤በዚሁ የክፉ ፋሽሽታዊ የጭቆና የወያኔ ስርአት ሆነህ ሳትረበሽ ሳትፈራ በአስደናቂ ጥበብና ዘዴ በተሞላበት የአንድ ሰው ደም ሳይፈስ ከአዲስ አበባ ቤተ መንግሥት ሙሉ በሙሉ ነቅለህ ጓዙን ሳይዝ ወደ መቀሌ በለሌት ሸሽቶ እዛው እንዲመሽግ ያደረከው ጀግና የሙያና የጥበብ ህዝብ ነህ፡፡

ህወሓትና ከሚከተለው ፋሽሽታዊ አገዛዙና ስርአቱ በአንተ አልገዛም፤ኢትዮጵያ ሃገሬም በባንዳው ቅጥረኝው ወያኔ ሉአላዊነትዋ አይደፈርም ኢትዮጵ አንድ ህዝብ ነው!! ባዩ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ሃይልና ጥበቡ ተማምኖ ከምኒሊክ ቤተ መንግሥት በማባረር ፋሽሽታዊ ስርአቱና አገዛዙ ተሸክሞ በቀንና በሌሊት ፈርጥጦ መቀሌ ምሽጉ የገባው።

ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት ዳግም ወደ ምኒልክ ቤተ መንግሥት እንድይ መለስ አድርጎ በርግዶ የጣለው ኢትዮጵያ ታላቅ ህዝብ ነፃነትህ ተቀዳጀ፤ከወያኔ ፋሽሽታዊ አገዛዝ ነፃ ወጣ።ኢትዮጵያ እናትህ ሃገርህ ከለላህ ሂወትህ መኖሪያ ናት አሁንም በጥብቅ ጥበቃት፤ መከታና ጋሻ ሁነህ ቁሙላት፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!! ክቡር የሃገርና የኢትዮጵያ ህዝብ መሪ ጥቅላይ ሚኒስትር፣
ዶ/ር አብይ አህመድ!!

ዛሬ ጀግና ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ መራራና ከባድ መስዋእትነት ከፍሎ በእውን በላው ፋሽሽት ናዚ (ወያኔ) የህ ወ ሐ ት አገዛዝ ስርአት በድል አድራጊነት ድሉን የተጎናጵፈ የተቀዳጀ ታላቅ ህዝብ ነው፡፡ ይህ የማፍያ የሌቦች ስብስብ ከአዲስ አበባ ቤተ መንግሥት ሸሽቶ ትግራይ

መቀሌ ቢመሽግም ዞሮ ዞሮ የትግራይ ህዝብ ለድርብ ድርብርብ የባርነት ሰንሰለት መፍትሄ የሌለው የባርነት ሲኦል ወደቀ 46 አመት በህወሃት የባርነት ቀንበር የማቀቀ ህዝብ ትግራይ ነው፤ 17 የትግል ዘመኑ አመቱ ያየው ያሳለፈው ክፉና ዘግናኝ ጨለማ ነው፤ በሰው ልጅ ሊደረጉ የማይገቡ ጭካኔ ህወሃት ሠርቷል፤ ተገደለ፤ ታሰረ በቶርቸር ተሰቃየ፤ ሃብት ንብረቱ ያለችውን ጥሪት በህወሃት እየተወረስ ቤቱ ፈረሰ፤ እቃ ተሸካሚ አመላላሽ እሱ የቆሰለ የታመመ የወያኔ ታጋይ ቃሬዛ ተሸካሚ፤መልእክት አመላላሽ ተላላኪ እሱ መንገድ ጥራጊ እሱ ስንቅ አቅራቢ የታጋይ ስንቅ ተሸካሚ እሱ ቤተ ክርስትያን እንዳይሳለም የታገደ ህዝብ የልጆቹ ሰርግ የታገደ ተስካርን የተክለከለ ህዝብ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ካለ የህወሃት ፈቃድ በስተቀር በጥብቅ የተከለከለ ህዝብ ወዘተ ወዘተ በትግራይ ህዝብ ስም የነገዱ፤ መንግሥት ከሆኑም በትግራይ ህዝብ ሸቅጥዋል አጭበርብረዋል የሃገርና የህዝብ ሃብት ንብረት ሙሉ በሙሉ ዘርፈዋ ሰርቀዋል ወያኔዎች ለምሳሌ እንይ ኢ ፈ ር ት *(ት እ ም ት) እንዳል በሙሉ ከኢትዮጵያ ህዝብ የሃገር ሃብት ዘርፈው ያቋቋሙ ግዙፍ ተቋም ነው* የትግራ ህዝብ ሃብት አይደለም የትግራይ ህዝብም ቢሆን ይህን ግዙፍ ተቋም ለማቋቋም በተአምር አይችልም አቅም ሃብት የለውም፤ በትግራይ ህዝብ ስም ግን ወያኔዎች ነገዱበት ሸቀጥበት ሌሎች ብዙ የንግድ ተቋማት አሉ በትግራይ ህዝብ ስም ያቋቋሙት ለምሳሌ የትግራይ ልማት ማህበር ተብሎ የሚታወቅ የትግራይ ህዝብ ማህበር ሳይሆን የሰብሃት ነጋ የቤተ ሰብ ድርጅት ነው፤ የትግራይ ህዝብ ግን አያውቀዉም፡፡ የህወሃት ሌቦች በህዝቡ ስም አሁንም ይሰሩበታል! ህወሃት ለትግራይ ህዝብ እንደሰው ሳይሆን እንደ ገዛው የግል አገልጋይ አሽከር የሚመለከተው የመናገይ መብቱ በጥብቅ የተከለከለ ህዝብ ከ45 በላይ በክፉ አሰቃቂ ሁኔታ በዚህ የባርነት ሲኦል በህወሃት ፋሽሽታው የባርነት ሸንሸል ታስሮ እየተገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ከዚህ አሰቃቂ የወያኔ አገዛዝ ለመገላግል ነጵነቱ እጅግ የሚፈልግ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ሰርቶ መኖር በፈለገበት በሃገሩ ኢትዮጵያ መኖር የሚፈልግ ህዝብ ነው፡፡

አሁን ግን ችግሩ መከራው የባርነቱ ፋሽሽታዊ የህወሃት አገዛዝ ስለ መረረው በተለይ ወያኔ መቀሌ ከመሸገ ጊዜ አንስቶ ህዝቡ በራሱ ፍላጎትና ተነሺነት በእንደርታ፤ በሽሬ እንዳሥላሴ፤ በተምቤን፤ በአዲግራት፤ በሁለት አውላእሎ፤ ወዘተ በየቦታው በህቡእ በመደራጀት ከወያኔ ህወሃት የባርነት ስርአትና አገዛዝ ሰባብሮ ለመላቀቅ ሃርነቱ መልሶ የቀድሞ ኢትዮጵያዊ ክብሩን ለመያዝ በቃኝ ብሎ ስለተነሳ ፈንቅል በሚል ስያሜ የትግራይ ክፍለ ሃገር ህዝብ የህ ወ ሃ ት የጭቆና የባርነት አገዛዝና ስርአት ከስር መሰረቱን ነቃቅሎ ለመቅበር ለመደምሰስ የህ ወ ሃ ት ህልውና ዳግም ለማየት ስለማይፈልግ ተመልሶም እንዳይታይ ወስኖ በቁርጥ ስለተነሳ፤ በፈንቅል ድርጅት የተሰባሰበው፡፡

ፈንቅል ያለበት ምክንያትም ከታሰርክበት የ46 አመታት የህ ወ ሃ ት (ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ) የባርነትና የጭቆና የአገዛዝ ስርአት ሰባብረህ፣ አንተነትህ ኢትዮጵያነትህ ሃገርነትህ ኢትዮጵያዊነትህ ተቀዳጅ ማለት ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ እጅጉን ድጋፍና ትብብር ይፈልጋል፡፡ሁሉ ኢትዮጵያዊም ይህን የትግራይ ህዝብ ጥሪ ተቀብሎ አስፈላጊው ድጋፍና ትብብር ማለትም በሃሳብ፤በምክር፤በሞራል በተለያዩ እርዳታዎች የኢትዮያዊነትና ወገናዊ ትብብርም ስለሆነ የግዴታም ግዴታ ነው፡፡ ክቡር ጥቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እርስዎ ኢትዮጵያ ሃገራችን ከ2010 አ ም መምራት ከጀመሩበት ጊዜ በሃገራችን የሰው ልጅ መብት እፎይታ የመናገር መብት ፍቅርና መተሳሰብ የታየበት የመጀመሪያ ታሪካዊ ምእራፍ ነው፡፡ክቡር ሚኒስተር እርስዎ የኢትዮጵያ ህዝብና ኢትዮጵያዊነት ከሃቅ ከእውነት ከልብ ይወዳሉ ያፈቅራሉ እኔ በእርስዎ ኮራህ ተደሰትኩም፤ መሪ ማለትም ይህ ነው፡፡ ክቡር የኢትዮጵያ መሪ እርስዎ

በትግራይ ህዝብ ጥሩ አመለካከት አለዎት እጅጉም ይወዱታል ያከብሩታል ክብሩና መብቱ እንዲ ከበርለትም ያለዎት ፍላጎት እጅግም የላቀ ነው፤ከዚሁም ተነስቶ የትግራይ ህዝብ በትልቁ እውነተኝ መሪው አብይ አህመድ ያከብራል እጅግ አድርጎ ያምናል፡፡ ከህ ወ ሐ ት (ወያኔ) ጭቆና የባርነት አገዛዝና ስርአት ከአንድ ለአምስት ጥርናፈ የባሪያ ስርአት ለመላቀቅ ለመገላገል ፍላጎቱ ከፍታው ሰማይ የደረሰ ነው፤ ክቡር የኢትዮጵያ ጥቅላይ አዛዥና መሪ ዶ/ር አብይ አህመድ በእግዚአብሄርና በኢትዮጵያ ህዝብም ለዚሁ ሃላፊነትና መሪነት በቅተዋል የኢትዮጵያ ህዝብም በእርሶ ላይ እጅግ የላቀ እምነት አለው፤ ከዚሁ እምነት ብቃት መሪነትዎ በመነሳት የሚወዱት የትግራይ ህዝብዎ ለ46 አመታት በህ ወ ሃ ት (ወያኔ) መሳፍንትና ባንዳ ዲቃልዎች ወረበላዎች የተሰቃየው የትግራይ ህዝብ ከነዚሁ ባንዳ የማፍያ ዘራፊዎች በሃይለ ጥበብዎ ይገላግሉት ይህን ለማድረግ ድግሞ የመሪነት ሃላፊነት ግዳጅዎ ነው፤ የትግራይ ህዝብ ከወያኔ የ46 አመታት የባርነት፣ መስፍናዊ፣ ፋሽሽታዊ፣ አገዛዝ በማውጥት ያታሪካዊ ሃርነቱ፤ ክብሩ፤ ማንነቱ መልሶ እንዲያገኝ ያድርጉት፡፡

የተከበራችሁ የብልጽግና ፓርቲ አመራርና አባላት በሙሉ ወያኔ ህ ወ ሐ ት በትግራይ ህዝብ ሲያደርሰ የነበረው ግፍ ሰቆቋ አረሜናዊ ጭካኔ አሁንም በተግባር በትግራይ የባርነት አገዛዙና ስርአቱ አደራጅቶ አስፋፍቶ ቀጥሎበታል የትግራይ ህዝብ በወያኔ ፋሽሽታዊ የሲኦል ነበልባል በባሰ ክፉ ደረጃ ወድቀዋል ይህም ሁሉ ከእናንተ የተሰወረ አይደለም በጋህድ የምታዩት ዘግናኝ ነው፡፡አሁን የትግራይ ህዝብ ሁሉ በአንድነት ተሰባስቦ የህ ወ ሐ ት (ወያኔን) የባርነት የሲኦል አገዛዝ ይብቃኝ ብሎ ፈንቀል በሚል ስያሜ ተደራጅቶ የሚመሩት መሪዎች ሰይሞ በወያኔ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ብሎም ሙሉ በምሉ ለመደምሰስ ተደራጅቶ ተነስቶ በህ ወ ሃ ት ላይ ዘመቻው ጀምሮታል ይህ ትግል ግቡን ለማድረስ የእናንተ ኢትዮጵያዊነት ዙሪያ መለሽ ተብብርና ሁለንተናዊ ድጋፍና ግዴታም ጭምር እጅግ ወሳኝ ስለሆነ ፈንቅልን መተባበር ኢ ትዮጵያዊ ወገናዊ የዜነት ሃላፊነት ነው፡፡ የፈንቅል መሪዎችም በትግራይ ህዝብ የተረከባችሁት ሃላፊነትና ግዳጅ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ስፍራ ስለአለው በእግዚአብሄር ሰም የተቀበላችሁት በሃቅና እውነት ስሩ የትግራይ ህዝብም ከህ ወ ሐ ት የባርነትና የጭቆና አገዛዝ ገላግሉት መብቱ ሃርነቱን አስከቡሩለት፡፡ይህም የሚገኝ በመስዋእትነትና በጥንካሬ የትግል ተግባር ነው፡፡

ወያኔ በትግራይ ክልል የወያኔ መሪዎች ለተመራጭ አዘጋጀ? መብቱንስ ከማን አገኝቶ? ህጋዊነት የለዉም፤ የእብዶች ሤራ።

ውድ የትግራይ ህዝብ!! ወያኔዎ ክጭንቅላት አልወረዱም ለ46 አመታት በባርነት ጭቆናና ስቃይ የተሰቃየከው አልበቃ ብሏቸው አሁንም የትግራይ ህዝብ ለሰቆቃና መከራ ዘመን ሊዳረግ ነው፤አሁንስ በቃኝ በል!!
ወያኔ ህ ወ ሃ ት በነሃሴ ወር 2012 የሚያካሂድው በትግራይ ክልል ተመራጭ የባንዳ መሳፍንቶች አስመራጭ የባንዳ ተላላኪዎች ለነብሳቸው ያደሩ የፋሽሽቱ ህ ወ ሃ ት ጋሻ ጃግሬዎች ሰብስቦ ነሃሴ ወር 2012 አ ም መብቅያ ሊያካሂድ በዝግጅት እንዳሉ እናውቃለን፤ ይህ ህገ ወጥ የኢትዮጵያ

ህግና ስርአት የሉአላዊት ሃገር ህገ መንግሥት የማያከብር የማፍያ ባንዳዎች ተግባር ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም፤ ኢትዮጵያዊም አይደለም፤ ከሃገር ህገ መንግስት ውጭ የሆነ ለክፉ አደጋ የሚዳርግ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ያልተቀበለ የተቃወመም ደግሞ ራሱ ድርጅቱ ህወሃት ነው፤ የኢትዮጵያ ህዝብና የሃገር ጥላቻ ያለበት ወያኔ ነው፡፡ ህገ ወጥ ወያኔ ህ ወ ሐ ት በኢትዮጵያና በህዝብዋ እጅግ ክፉ አደጋ የያዘ ጥላቻ ያደረበት ድርጅት ነው ፤ የዚህ ድርጅት ህልውና ባጭር ጊዜ መጥፋት አለበት፤ ስለሆነም ሊያካሂደው የክልሉ መሪዎች ተመራጭ የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ደንብና ስርአት ያልተከተለ ከኢትዮጵያ ምርጭ ቦርድ ኮሚሽን ተቀባይነት የሌለው ውድቅ የተደረገው ወያኔ በትግራያ አካሂደዋለህ ለሚለው የትግራይ ህዝብም በህገ ወጥነቱ ያተቀበለው ህገ ወጥ መሆኑም የተገነዘበው ነው፤ ስለሆነም የትግራይ ክዚሁየወያኔ የተንኮል ሴራ አተሳተፍ በቃኝ በል እነዚህ ፋሽሽቶች ባንተ ስም ንግደዋል ዘርፈዋል ላንተም ገድለዉሃልፋሽሽታዊ ግፎች ባንተ ላይ አካሂደዋል አሁን ባቀዱት የማጭበርበ ተግባር አሳፍራቸው አትቀበለው ፈንቅልና ሌሎች ድርጅቶች የትግራይ ህዝብ በዚሁ እንዳይሳተፍ ለማድረግ የማስተባበር የመከላከል ሃላፊነቱ መውሰድ ግዴታ አለባቸው፡፡ ወያኔ እንኳንስ ትግራይ መምራት ቀርቶ በመሬትዋም መኖር አንፈቅድለትም፤ መጥፋትና መደምሰስ አለበት፤ ነበር ሆኖ እንዲቀር ማድረግ የሁላችን የግዴታ ግዴታ ነው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ!!
ገብረመድህን አርአያ ( የህወሃት፤ ነባርታጋይ ነበር)
አውስትራሊያ፤ ፐርዝ

LEAVE A REPLY