ኤታማዠር ሹሙ ልዩ ሃይል በህገ መነግስቱ ድጋፍ የለውም አሉ

ኤታማዠር ሹሙ ልዩ ሃይል በህገ መነግስቱ ድጋፍ የለውም አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሀገር ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመከላከል የተሟላ ዝግጁነት እንዳለ የመከላከያ ኢታማዦር ጀነራል አደም መሐመድ ገለጹ።

ሠራዊቱ በውጪም በውስጥም ሊቃጡ የሚችሉ፣ በተለይም ሀገራችንን ቀጣይነት ወዳለው ትርምስ እንድትገባ የሚያደርጉ ኃይሎችን በመቆጣጠር እና በመግታት ስኬታማ ሥራ መሥራቱ ታውቋል።
“ዘየመከላከያ ሠራዊቱ በብሔር ተከፋፍሏል በሚል ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ በማራገብና የተለያዩ ስሞችን በመስጠት ሠራዊቱ ከተልዕኮው እንዲዘናጋ ለማድረግ የሚጥሩ አካላት መኖራቸውን የጠቆሙት ኢታማዦር ሹሙ፤ እውነታው ግን የመከላከያ ሠራዊቱ አንድነቱን አጠናክሮ የሚሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ መሆኑ ነው ብለዋል።
የመከላከያ ሠራዊቱ ወቅቱ የሚጠይቀውን ትጥቅ እና ቴክኖሎጂ፤ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም በሚፈቅደው ልክ እያሟላ እንደሚገኝ የገለፁት ጀነራል አደም መሐመድ፤ ሁሌም ቢሆን ለየትኛውም ተልእኮ የዝግጁነት ሥራዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ከመጠቆማቸው ባሻገር፤ “ሊያጋጥመን የሚችል ጠላትን ግምት ውስጥ በማስገባት የሠራዊታችን ዝግጁነት ተቋርጦ አያውቅም። ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት እየሰለጠነ፣ እየታጠቀ፣ ማንም ወገን ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለማድረስ እንዳያስብ፣ ካሰበም ደግሞ የመከላከል ሁኔታ አይቶ ወደ ጥቃት እንዳይገባ ዝግጅት ተደርጓል።” ሲሉም በቂ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተያያዘ የክልል የፀጥታ ኃይሎች የትጥቅ ደረጃ ያለመወሰን የአሠራር ችግር መኖሩን የሚጠቁም መሆኑን የገለጹት ኢታማዦር ሹሙ፤ ሆኖም እነዚህ የፀጥታ ኃይሎች ከባድ የጦር መሣሪያ ታጥቀዋል የሚያስብል ነገር አለመኖሩን አስታውቀዋል።
የሀገርን ዳር ድንበር እና ሉዓላዊነት የመከላከል እና የመጠበቅ ኃላፊነት የሀገር መከላከያ ሠራዊት መሆኑን ቢሆንም፤ የሀገር ውስጥ የፀጥታ ሁኔታን በፌዴራል እና በተዋረድ ያሉ የፀጥታ መዋቅሮች እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።
 በክልሎች ልዩ ኃይል የሚባል ኃይል መፈጠሩን፣ በተለይ ደግሞ በአንዳንድ ክልሎች ልዩ ኃይሉ አቅም እየፈጠረ የመጣበት አዝማሚያ መፈጠሩን የጠቆሙት ጀነራል አደም መሐመድ፤ ልዩ ኃይል ከሕገ-መንግሥቱ አንፃር ሲታይ ሕጋዊ ማዕቀፍ የለውም ብለዋል።

LEAVE A REPLY