ግልጽ ደብዳቤ ለኦሮሞ እናት እና አባቶች በያላችሁበት || ፍካ ወልደጻዲቅ

ግልጽ ደብዳቤ ለኦሮሞ እናት እና አባቶች በያላችሁበት || ፍካ ወልደጻዲቅ

የተከበራችሁ ኦሮሞ እናትና አባቶቼ  በያላችሁበት ከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ፡፡ እንደምን አላችሁ? ደህና ናችሁ?

እንዲህ ህልም ይሁን ፊልም ቅጡ በጠፋበት በዛሬየኢትዮጵያ የእብደት ዘመን ላይ ሆኜ የእናንተ ድርሻ ጉልህ የነበረበትን ደጉን የልጅነ ዘመን ሳስብ ደስታዬ ወሰን ያጣል፡፡ አንዳንዴም እዛው ሀሳብ ላይ ቆሞ መቅረት ያምረኛል፡፡ ይብላኝ ያንን የመሰለ ፍቅርና መከባበር ማየት ላልታደሉት የዘመኑ/የብልፅግና ልጆች፤ ደግሞም ወዮላቸው ለእነኛ አይተው አላየንም ሰምትው አልሰማንም ብለው ለካዱ የበሉበትን ወጭት ሰባሪች፡፡  

እናንተስ ምን ይሰማችሁ ይሆን? እውነት እውነት እላችኋለው ትክክለኛ ስሜታችሁን ለማወቅ  ከልቤ እጓጓለሁ፡፡ ይሄ ሁልጊዜ ችግር ከተፈጠረ በኋላ ታስቦበት ለፖለቲካ፣ ለሚዲያ፣ ለካሜራ፣ ለውሎ አበል  እና ለበሬ ፍጆታ በስማችሁ የሚዥጎደጎዱትን ባዶ የይቅርታና የተስፋ ቃላት ሳይሆን እውነተኛውን ስሜታችሁን ማወቅ ነው የምፈልገው፡፡

እስቲ ልጠይቃችሁ

ድሮ በደጉ ዘመን ልጆቻችሁ ከጎረቤት ልጆች ጋር ሲጣሉ “ከመልካም ጎረቤቶቼ ልታቀያይሙኝ” ብላችሁ የምትገስጿቸው ትዝ ይላችኋል? አንቺ ትብሽ አንተ ትብስ ተባብላችሁ ክፉና ደግ አብራችሁ ያሳለፋችኋቸው  ወላጆቻችንም ቢሆኑ እኮ የእናንተን ልጆች ከነካን የቁጣ መአት ነበር የሚያወርዱብን፡፡ ኧረ ዱላም ያቀምሱን ነበር፡፡

ያኔ የአንዱ ልጅ ሲያጠፋ ሌላው አይቶ ዝም አይልም ነበር፡፡ የዚያ ዘመን ወላጅ ባልወልደውስ ልጄ አይደል እንዴ?” “የእገሊት ልጅ ማለት ያው የእኔ ልጅ ማለት ናት” እያለ የሰፈሩን ልጅ ሁሉ በእኩል ዓይን እያ ነበር የሚያሳድገው፡፡   ባስ ሲልም ኩርኩም እና አርጩሜም አይቀርልንም ነበር፡፡ “ነበር እንዲሁ ቅርብ ኖርዋል ለካ?” አሉ እቴጌ ጣይቱ፡፡

እናንተ መልካም ኦሮሞ እናቶች እና አባቶች߹ ግን እንደው ለመሆኑ ዛሬ አገራችን ላይ በተለይ በአማራው እና በክርስቲያኑ ላይ ለተከፈተው ግልጽ ጦርነት አድራጊውም ፈጣሪውምየእናንተ የአብራካችሁ ክፋዮች መሆናቸው እንዴት? የሚል ጥያቄ አላጫረባችሁ? ምን ተሰምቷችሁ ይሆን? በበኩከህያዋንም፣ ከሙታንምንስሳም፣ ከግዑዙምከምግቡም፣ ከመጠጡም፤ ከነጩም፣ ከጥቁሩምከመንግሥትም፣ ከህዝብም፤ ከእራሳቸውም፣ ከምናቸውም ጋር ሲለተሙ የሚውሉ የጥፋት ሠራዊቶችን አፍርታችሁ ለአገር (ምን ለአገር ብቻ ለዓለምም እየተረፉ ነው) ገፀ-በረከት አቀረባችሁ ብዬ ለማመን በጣም ከበደኝ፡፡ አፈርኩ፡፡  ከእናንተ አብራክ ወጡ ለማትም ተናነቀኝ፡፡ ይህን ማሰብ በለጠ ያማል፡፡ ስቃን ያበዛዋል፡፡ ግን ደግሞ እውነት ነው፡፡ ስለዚህ ቢያንስ እራሴን ለማፅናናት እናንተ ይሄንን ጉድ አልሰማችሁም፤ አላያችሁም፤ ብዬ እራሴን ለማሳመን ወደድኩ፡፡ አልሰማችሁምአይደል?  አላያችሁም አይደል?

 እነኛ በዓለምም በሀዘንም ከጎናችሁ ሆነው የኖሩት አብሮ አደግ ወንድም እና እህቶቻችሁ የእኛ ወላጆች በእናንተው ፍሬዎችገጀራ ተከታትፈው ላይመለሱ መሄዳቸውን፤ ከዚያም አልፎ አስከሬናቸው የኦሮሞን አፈር እንዳይቀምሲከለከ አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡

አብራችሁ ቡና የጠጣችሁምጣቸው ያዋለዳችኋቸው፣ አራስ ቤት ያረሷችሁ፣ በደስታ አብራችሁ የጨፈራችበሀዘን እንባ የተራጫችሁ ድስት እና ሰፌድ የተዋዋሳችሁ፣ ሚስጥር የተካፈላችሁ፣ የተማከራችሁ ገበያ አብራችሁ የወረዳችሁ፣ ገበናችሁን የተሸፋፈናችሁ እናቶ በእንባ ጎርፍ አገሩን ሲሞሉት አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
ሰው ተዘቅዝቆ ሲሰቀል፣ የሰው አስከሬን እንደሽንኩርት ሲከተፍ፣ እንደእንጨት ሲፈለጥ፣ አንደዶሮ ብልት ተገነጣጥሎ ሲቀርብ፣ እንደበሬ ሥጋ በመንጠቆ ላይ ሲንጠለጠል፣ መንገድ ለመንገድ ሲጎተትና እንደ ቡሄ ችቦ ሲነድ አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
የነገ የአገር ተስፋ የሆኑ ወጣት ሴቶች ትምህርት ብለው ወተው በየመንገዱ እየታፈኑ ደብዛቸው ሲጠፋ፤ ሴቶች በባሎቻቸው ፊት ሲደፈሩና  የደረሱ ነፍሰ-ጡሮች በግፍ ሲገደሉ አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
ወላጆቻቸው ሳጥናኤልን በሚያስቀና ጭካኔ ተሰቃይተው ሲገደሉ በታዛቢነት ተቀምጠው ትምህርት እንዲወስዱ የተፈረደባቸው ህፃናት በመንፈስ ጭንቀት ሲሰቃዩ አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
ስንቱ ጥሮ ግሮ አዳሪ ምስኪን ደሀ የኦሮሞ ሀብት በዝባዥ የሚል ማዕረግ እየተሰጠው አንገቱ በልጆቻችሁ የጭካኔ ሰይፍ ሲቀላ፣ ንብረቱ ሲወድም፣ ድህነትም ብርቅ ሲሆንበት አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
ስንቱ ተወልዶ፣ አድጎ፣ ከጎለመሰበት ከታደለም ካረጀበት ቀዬ መጤና ሰፋሪ እየተባለ ሲሰደድ አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
ስንቱ ላቡን አንጠፍጥፎ ፈራው ንብረት ኑሮውን ከማሸነፍአልፎ ለአገር ኮኖሚ እንዳቅሙ ሊያበረክት ደፋ ቀና ወፌ ቆመች እየተባለ ሲዘፈንለት ለጥፋት እንጂ ለሥራ ያልታደሉ ንብረቱን ዶግአመድ አድርገው መናጢ ደሀ ሲያደርጉት አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
ስንት አብያተ ክርስቲያናት ከነቀሳውስታቸው ተማግደው እሳቱን ጨካኞች ሞቁት አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
ገነባ ፈርስ፤ መሠረተ-ልማት፣ ከማንነታችን ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸው ሀውልቶች ሌላም ሌላም ሲፈራርሱ አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
ዛሬ ልጆቻችሁ አፋቸውን የሚፈቱት አማራንና ይቺን የፈረደባትን ምስኪን እናት አገር በመስደብ እንደሆነ  አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
የአገር ውስጥ አልበቃ ብሏቸው  በዘመንዋ ኃያላን መንግሥታትን ያንበረከከች አገር ዛሬ የእናንተ ልጆች ደርሰው በዓለም አደባባይ ሲያዋረደዋት አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
አብሮ አደጎቻችን የእናንተ ልጆች  ያሳለፍነውን መልካም ዘመን ረስተው ዛሬ ለነፍስ ሲያፈላልጉንነ (ስድቡንና ማሸማቀቁንማ ለደነዋል) አላያችሁም፤ አልሰማችሁም፡፡
ኦሮሞ አቃፊ ነው ይባላል፡፡ እኔም በዚህ አምናለሁ፡፡ ምክንያቱም እናንተን በቅርብ እያየሁ ነው ያደኩት፡፡ ነገርግን ልጆቻችሁ ማቀፍና ማነቅ ሲምታታባቸው በደቦ ወጥተው ግለሰብ ሲጨፈጭፉ አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
በየመገናኛ ብዙኃኑ አፋቸውን ሞልተው ምንጩም ጭብጡም የማይታወቅ በጥላቻና በማን አለብኝነት የታጨቀ አፈ̵ታሪክአንዳዴምሉባልታ ታሪክ እያሉ ሲግቱን (እውነተኛ ታሪክ እንዳንለው እውነት የለበትም፤ የፈጠራ ታሪክ እንዳንለው ጥበብ የለበትም) አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡
ከሌላ ብሔር የተጋባ ኦሮሞ እንዲፋታ፣ የትኛውም ኦሮሞ ከሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋር ምንም ግንኙነት እንዳይኖረው ወዘተ. እየባለ ሲለፈፍ አላያችሁምአልሰማችሁም፡፡

እንዴ! እኛ እኮ ጨነቀን! እርግጥ ነው ይህን ሁሉ ጉድ ባትሰሙና ባታዩ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን ተወደደም ተጠላም ይህን ሁሉ ሳጥናኤልን ያስቀና ጭካኔ የፈፀሙት ልጆቻችሁ ናቸው፡፡ ጥያቄው እነኚህ ወንበዴ ልጆች ያንን ሁሉ ጥፋት ፈጽመው መተው ቤታችሁ አስገብታችኋቸዋል? ምግብ ሰጥታችኋቸዋል? አሳድራችኋቸዋል? አልተፀየፋችኋቸውም? የሰው ደም ጠምቷቸው ሲክለፈለፉ ስታዩ ምን ተሰማችሁ? እናቶች እውነቱን ንገሩኝ “ምነው ባልወለድናቸው፤ ማህፀናችን ውስጥ ውኃ ሆነው በቀሩ” ብላችሁ አለተመኛችሁም?

አባ ገዳዎችስ የት ነው የምትኖሩት? ይሄ ሁሉ ግፍ ሲፈፀም እንዴት ነው ወታችሁ ልጆች ተገቢ አይደለም፣ በእኛእሬሳ ላይ ያላላችሁት? ከመንግሥት ጋር በመናበ ለሚዲያና ለካሜሪ ብቻ ነው እንዴ የምትወጡት?

የእኛን ልጆች አይወክሉም፤ ቄሮን አይወክሉም፤ ከአጠቃላይ ከኦሮሞ ወጣት ቁጥር አንፃር ሲታይ ይህ የጥፋት ሠራዊት ቁጥሩ በጣም አነስተኛ ነው፤  አናውቃቸውም ከሌላ አካባቢ ነው የሚመጡትእያላችሁም የተለመደና የማይታመን ምክንያት ድርደራ ውስም አትግቡ፡፡ አያስፈልግም፡፡ እኛም ድፍን ኦሮሞ ወጥቶ ይህን ነውረኛ ድርጊት ፈፀመ አላልንም፡፡ በእርግጥ በድርጊቱ የሚሳተፉት ወጣቶችና ጎልማሶች አገር ለማሸበርም ቁጥራቸው ከበቂ  በላይ ነው፡፡ ይልቁንስ ነገር ማለባበሱንና የቁጥርና የመጠን ጨዋታውን ትተን ሀቁን እንጋፈ፡፡ አጥፊዎቹ የእናንተው ልጆች የእኛም እህትና ወንድሞች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አለቀ፡፡

በእርግጥ የጽሁፌ ዓላማ የልጆሁን ሀጥያት በመዘርዘር እናንተን ለማሳጣትና ለማሳቀቅ ሳይሆን መፍትሄውም እናንተ ጋር እንደሆነ ለመጠቆም ነው፡፡

ለአንድ ልጅ እድገት ቤተሰብ፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም ያደጉበት ማህበረሰብ እንደአጠቃላይ የየራሳቸው ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ የሐይማኖት ተቋማት የሚለውን ብዙ ነገር ስለሚያማዝዝ ለጊዜው ባልነካካው መርጣለው፡፡ የትምህርት ሥርዓቱን በተመለከተ ግን ሁሉንም ተማሪ በእኩል የበደለው ስለመሆኑ ብዙ ተብሏልና መድገም አያስፈልገኝም፡፡ ሌላው ተጠያቂ መንግሥት ነው፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ እኛ ኢትዮጵያውያን መንግሥት አይዋጣልንም፡፡ ሁሉ ጊዜ ትሻልን ትተን ትብስን ስናገባ ነው የምንገኘው፡፡  አሁንማ በትብስም ከተገላገልን ጥሩ ነው፡፡ ገና በሁለት አመት ከመንፈቋ ትባባስም አንሷታል፡፡ ሲጀመር ኢ.ህ.አዴ.ግ ማለት በኢትዮጵያ ላይ የመጣ አንዳች ምጣት እንደሆነ ከእናንተ የተሸሸገ አይደለም፡፡ የበኩር ልጁ የሆነው ብልጽግናም ቁርጥ እሱን ነው፡፡ እንደውም ለእናንተ ትንሽ ልቡ ይራራል ልበል!?

ሕግ ያለው አዲስ አበባ ላይ ብቻ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም አድራጊ ፈጣሪነታቸው እዚችው እቴጌ ጣይቱ የቆረቆርዋት ከተማ ላይ ነው፡፡ እሳቸውን እንቅልፍ የሚነሳቸው ጉዳይ የአዲስ አበባ ሕዝብ ለመብቱ መደራጀቱ እንጂ ኢትዮጵያዊያን በገዛ አገራቸው መብት አልባ ሆነው በዘርና በኃይማኖት መጨፍጨፋቸው አይደለም፡፡  የእሳቸው ነገር እንኳን ተከድኖ ይብሰል ብለን ማለፍ ነው የሚሻለው፡፡ ሰውየው ከዋና ከተማዋ ውጪ አቅምም አቋምም እንደሌላቸው ከዚህ በፊት አዲስ አበባ ላይ ልጃችሁን ጀዋርን አስፈራርው፣ እናንተ ክልል ሲመጡ ደግሞ ያን ለማስተባበል ሲኮለታተፉ ሳትታዘብዋቸው አትቀሩም፡፡ እና በአጭሩ ሰውየው የኢትዮጵያ ሳይሆኑ የአዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው (ይህ ያንሳቸዋል የሚል ካለ ያልተዋጣለት ቲያትረኛ የሚል ማዕረግ ሊመርቅላቸው ይችላል)፡፡ ስለዚህ እሳቸው ከሚመሩት መንግሥት ይሄነው የሚባል መፍትሄ መጠበቅ ጅልነት ይመስለኛል፡፡

ከዚያ ይልቅ ለጊዜው አቅማችን የሚፈቅደው ቤተሰብ ከዚያም አልፎ ማህበረሰብ የሚለው ላይ ማተኮር ይመስለኛል፡፡ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ፡፡ በልጆች አስተዳደግ ላይ ቤተሰብ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስድ አያጠያይቅም፡፡  አንድ ሥነ-ምግባር የጎደለው ልጅ/ሰው “አሳዳጊ የበደለው” የሚባለው ለዛ ግለሰብ ምግባረ-ብልሹነት የአሳዳጊዎቹ ድርሻ የጎላ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ አይደል? ለዚህ ነው የልጆቻችሁ ሥርዓት-አልበኝነት፣ የጭካኔና የብልግናን ክብረ-ወሰን መስበር፣ በበታችነት ስሜት መወራጨት፣ በፈጠሩት ተሪክ ተጠልፈው መውደቅ ከዛም አልፎ እናንተን ጨዋዎቹን ወላጆቻቸውን ማሰደብ እጅግ አድርጎ ያንገበገበኝ፡፡

ድፍረት አይሁንብኝና ጥቂት ጥያቄዎችን ላንሳ፡፡ የዚህን ሁሉ ችግር ምንጭ ለማወቅ ሙከራ አርጋችሁ ይሆን? ልጆቻችሁን እንዴት ነው የምታሳድጉት? እነዚህ ዛሬ ሰው ገለው በአስሬን እቃእቃ የሚጫወቱ ልጆች ነገ ለእናንተስ ይመለሳሉ ብላችሁ ታምናላችሁ? መጨረሻቸው እንደማያምር ከወዲሁ አልታያችሁም? ለመሆኑ ትመክሯቸዋላችሁ? ሲያጠፉ ትገስጿቸዋላችሁ? ይሰሟችኋል? ይታዘዝዋችኋል? የጋሞ አባቶች በልጆቻቸው ዘንድ ያላቸውን ከበሬታና ተሰሚነት አይነት እናንተ በልጆቻችሁ ዘንድ አላችሁ? ካላችሁ እሰየው! ከሌላችሁ ግን ለምን ብላችሁ እራሳችሁን መጠየቅ መልካም ይመስለኛል፡፡

መቼስ አብዛኛው የኢትዮጵያ ልጅ በከረሜላ እና በአይስክሬም ሳይሆን በተረት እንደሚያድግ ይታወቃል፡፡ ተረት ደግሞ ዓላማው ማዝናናት ብቻ ሳይሆን በተለይም ማስተማር፤ አእምሮን በመልካም ነገር ማነፅ ነው፡፡ ፈጣሪን ስለመፍራት፣ ከሰው ጋር አብሮ ስለመኖር፣ ስለ አገር ፍቅር፣ ስለሥራ ክቡርነት፣ ስለትምህርት አስፈላጊነት የመሳሰሉት ጉዳዮች በተረት ውስጥ የሚካተቱ ዋና ዋና ጭብጦች መሆናቸውን ለእናንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ስለዚህ ተረቶቻችሁን መለስ ብላችሁ ቃኝዋቸው፤ የዘፈኖቻችሁንም ይዘት ተመልከቱ፤ የልጆች  አስተዳደግ ሥርዓታችሁን መርምሩ፤ የግጭት አፈታት ሥርዓታችሁንም ፈትሹት፡

እንደኔ እንደኔ መፍትሄው ያለው እናንተው ጋር ነው፡፡ ግድ የላችሁም ውስጣችሁን ተመልከቱ፡፡ የቱጋር ነው ክፍተት የተፈጠረው? እስቲ ሰብሰብ በሉና ተመካከሩ፤ ተወያዩ፡፡ የአባ መላ ልጆች መላ ፍጠሩ፡፡

እስከዛው ትላንትን አፍቅሬ፣ ዛሬን ጠልቼ፣ ነገን ፈርቼ ምላሻችሁን በጉጉት እጠባበቃለው፡፡

አክባሪያችሁ 

LEAVE A REPLY