ህወሓትን ለመጣልና ሰልፍ ለማድረግ ሞክረዋል የተባሉ የትግራይ ወጣቶች ላይ ክስ ሊመሠረት ነው

ህወሓትን ለመጣልና ሰልፍ ለማድረግ ሞክረዋል የተባሉ የትግራይ ወጣቶች ላይ ክስ ሊመሠረት ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከትግራይ ሕዝብ የሚቀርብበት ተቃውሞ እየጨመረ የመጣው ህወሓት በሚቃወሙት አካላት ላይ የሚወስደውን የኃይል እርምጃ  አጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።

ይህን ተከትሎም በመቀለ ሕገወጥ ሰልፍ ሊያካሂዱ ሲሉ ተይዘዋል የተባሉ ዘጠኝ ወጣቶች ላይ ከሠባት ቀን በኋላ ክስ ሊመሰረት መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ህወሓት አመፅና ሰልፍ ሊያካሂዱ ነበር  በሚል ወጣቶቹ በቁጥጥር ሥር ከዋሉበት ጀምሮ የትግራይ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መቆየቱን ትናንት ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ፤ ምርመራውን በመጨረሱ ፋይላቸውን ክስ እንዲመሰረት ወደ ዐቃቤ ሕግ ማስተላለፉን ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው እየታየ የሚገኝበት የመቀለ ከተማ ቀዳማይ ወያነ ፍርድ ቤትም ዘጠኙን ወጣቶች እስር ቤት እንዲቆዩ ያዘዘ መሆኑንም ቢቢሲ ዘግቧል።
በትግራይ የክልሉን መንግሥት ለመጣል የሚያነሳሳ መፈክር ይዛችሁ ተገኝታችኋል፣ በሚል በቁጥጥር ሥር የዋሉት እነዚህ ዘጠኝ ወጣቶች ትናንት ለሦስተኛ ጊዜ ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት።
ወጣቶቹ ከ46 ቀናት በፊት፣ ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ በመቀለ የሮማነት አደባባይ ላይ መንግሥትን በኃይል ለመጣል የሚያነሳሳ መፈክር ይዘው መገኘታቸውንና ያልተፈቀደ ሠልፍ ለማካሄድ ሲወጡ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው መግለጫ መስጠቱ አይዘነጋም።
በጊዜው ተጠርጣሪዎቹ በ48 ሰዐት ውስጥ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም፣ ፖሊስ በተደጋጋሚ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በመጠየቅ ከ46 ቀናት በላይ በእስር እንዲቆዮ ያደረጋቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት ወቅትም ችሎቱን ማንም እንዲታደም አልተፈቀደም።
 ከችሎቱ በኋላ የሚመለከታቸውን በማናገር መረዳት እንደቻለው ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ በመጨረስ ጉዳያቸውን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን ተከትሎ በዚህም ከሠባት ቀናት በኋላ ክስ እንደሚመሠረትባቸው ታውቋል።
ወጣቶቹ ‘ፈንቅል’ ከተባለው እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት እንደሌላለቸው መናገራቸውንና ቡድኑም ይህንኑ ማረጋገጡን ቢቢሲ መረዳት ችሏል።
ዘጠኙ ወጣቶች በሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ ላይ የክልሉን መንግሥት በመቃወም ሕገወጥ የተቃወሞ ሰልፍ ሊያካሂዱ ነበር በሚል በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ቆይተዋል

LEAVE A REPLY