ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ህወሓት በትግራይ ክልል ሊያካሂደው ያቀደውን ሥድሥተኛው ዙር ክልላዊ ምርጫን ጳጉሜ 4/2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ።
ይካሄዳል የባለለትና ከጅምሩ ውዝግብ ያስነሳውን ምርጫው ለማካሄድ ከአራት ሳምንታት ያነሰ ጊዜ የቀረ ሲሆን በዚህም መሰረት የመራጮች ምዝገባ ቀን ፤ ከነሐሴ 15 አስከ 22/2012 ዓ.ም እንደሚከናወን፣ ሁለት ተጨማሪ የመጨረሻ የምዝገባ ቀናትም እንዳሉ የክልሉ የምርጫ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ፀሐየ መረሳ ተናግረዋል።
የምርጫ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫው የሚያካሂዱት ቅስቀሳ ነሐሴ 29 ተጠናቆ፣ ከአዐራት ቀናት በኋላ ረቡዕ ጻጉሜ 4 ድምጽ የመስጫ ቀን እንደሚሆንም በቅርቡ የተቋቋመው ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሽን ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የህወሓት ድግስ አድማቂና አጃቢ ሆነው፣ በተፎካካሪ ፓርቲ ስም የተመዘገቡት ተወዳዳሪ ነን ባዮቹ ድርጅቶች፣ ምርጫው ሊካሄድ አራት ሳምንታት ያህል ቢቀረውም፤ ለምርጫው እንቅስቃሴ የሚያስፈልጋቸው የገንዘብ ድጋፍ እንዳላገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በምርጫው የሚሳተፉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቀደም ሲል በምርጫው ሥርዓት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ካነሷቸው ጥያቄዎች በተጨማሪ በበጀት ጉዳይም እንዳልተስማሙ እየተናገሩ ቢሆንም ውስጥ አዋቃዎች ግን እንደ ባይቶናና ሳልሳዊ ወያን የመሰሉትና ሌሎች በምርጫው የሚሳተፉ የትግራይ ክልል ፓርቲዎች አምላኪና አፍቃሪ ህወሓት እንደሆኑ በመግለፅ የሚያሰሙት ወቀሳና ቅሬታ የይስሙላ ነው ይላሉ።