ጎርጎራ፣ ወንጪና ኮይሻ የሚለሙበት “ገበታ ለሀገር” የተሰኘ መርሃ ግብር ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ...

ጎርጎራ፣ ወንጪና ኮይሻ የሚለሙበት “ገበታ ለሀገር” የተሰኘ መርሃ ግብር ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ሆነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዛሬ ይፋ የተደረገው የ”ገበታ ለሀገር” መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለኢትዮጵያ ብልጽግና አሻራቸውን የሚያኖሩበት መሆኑ ተነገረ።

ገበታ ለሀገር ይፋ በተደረገበት ወቅት የሀሳቡ ፈጣሪ ጠቅላይ ማኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ገንዘብ፣ እውቀት እና ጉልበት በማሰባሰብ ተፈጥሮን ሳናውክ ለዜጎችም ለውጭ ቱሪስቶችም የምትመች ኢትዮጵያን እንፈጥራለን” ሲሉ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ይፋ በሆነው ቅድመ ፕሮግራም መሠረት በገበታ ለሀገር መርሃ ግብር በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንታት የVVIP እና VIP የተከፈለበት የእራት ግብዣ እንደሚኖርም ይፋ ተደርጓል።
በዚህም መሠረት ሀገራዊ  ራዕይ የተሰነቀበት የእራት ግብዣው VVIP 10 ሚሊዮን ብር ሲሆን ፣ VIP 5 ሚሊዮን ብር እንደማከፈልበት ተነግሯል።
በገበታ ለሀገር መርሃ ግብር አማካይነት በኢትዮጵያ ብልጽግና ውስጥ ሁሉም ዜጋ አሻራውን እንዲያኖር በኢትዮ-ቴሌኮም አማካኝነት የአጭር የጽሑፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ዲያስፖራውም ድጋፍ እንዲያደርግ ገንዘብ የሚሰበሰብበት አካውንት የሚከፈት መሆኑ ታውቋል።
 ከገበታ ለሀገር ቢያንስ 3 ቢሊየን ብር ይገኛል ተብሎ ተብሎ የተገመተ ሲሆን፣ በሚገኘ በዚህ ሀብት ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚለሙ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY