የታከለ ኡማ አስተዳደር በሻሻመኔ ከተማ ለተጎዱ ሰዎች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የታከለ ኡማ አስተዳደር በሻሻመኔ ከተማ ለተጎዱ ሰዎች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢንጂነር ታከለ ኡማ አስተዳደር በሻሸመኔ ከተማ ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች 1.2 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጉ ተነገረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ እንዲሁም ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ያደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ 1.2 ሚሊየን ብር የሚገመት ነው ተብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶች እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ምክትል ሓላፊ ወ/ሮ ነፃነት ጉደታ ለሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ጉታ ሳቾሬ ፤ ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ብርድልብስ፣ የሕጻናት አልባሳት እና የምግብ መገልገያ ዕቃዎችን ማስረከባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ቢሮ ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY