ሐምዛ ቦረና የኮሮና ምልክቶች ቢታዮብኝም ሕክምናና ምርመራ ተከልክያለሁ ሲል ገለጸ

ሐምዛ ቦረና የኮሮና ምልክቶች ቢታዮብኝም ሕክምናና ምርመራ ተከልክያለሁ ሲል ገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የጃዋር መሐመድ ቀኝ እጅ የሆነውና በጽንፈኛ ብሔርተኝነቱ የሚታወቀው ሐምዛ አዳነ (ሐምዛ ቦረና)  የኮሮና ምልክቶች እየታየብኝ ነው ሲል ምርመራ እንዲደረግለት ችሎቱን ጠየቀ።

ከሐረር እስከ አሩሲ የአማራን ስምና ታሪክ የሚያጠለሹ የሀሰት ንግግሮችን፣ ጽንፍ የያዘ የኦሮሞ ብሔርተኝነትን የሚያሰርጹ ኹከት ቀስቃሽና የጥላቻ ንግግሮችን ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደጋጋሚ በመናገር የሚታወቀው ሐምዛ ቦረና፣ እያሳለው መሆኑን እና የኮሮናቫይረስ ምልክት እየታየበት መሆኑን በመጠቆም ፍርድ ቤቱ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግለት ትዕዛዝ እንዲሰጥለት አቤቱታ አቅርቧል።
ግለሰቡ አሁን ከታየበት ምልክት በተጨማሪ የደም ግፊትና የስኳር ህመምተኛ መሆናቸውን በመጥቀስ ለእነዚህ ህመሞች ሕክምና እንዲያገኙ ሁኔታ እንዲመቻችለትም ተማፅኗል።
በተያያዘ ዜና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማረሚያ ቤት የሚገኘው የኦ ኤም ኤን ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳ በበኩሉ፤ ከሌሎች ታሳሪዎች በተለየ መልኩ በስልክ ቤተሰቦቻችንን እንዳናገኝ ተደርገናል ሲል ቅሬታውን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
የተጠርጣሪዎች ጠበቆችም “ደንበኞቻችንን ለማግኘት በማረሚያ ቤቱ በተገኘንበት ወቅት ወደ ፍርድ ቤት ሄደዋል ተብለን ሳናገኛቸው ቀርተናል፣ እንዲሁም ደግሞ የደህንነት ካሜራው ምስላችንና ድምጻችንን የሚቀርጽ በመሆኑ እንዲስተካከል ፖሊስን ብንጠይቅም፣ ፖሊሶቹ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን በመግለጽ ሊያስተካክሉልን አልቻሉም። ስለዚህ ከደንበኞቻችን ጋር በሚስጥር ማውራት የምንችልበት ሌላ ክፍል ይሰጠን ወይም  ካሜራው ይነሳ” ሲሉ ችሎቱን ጠይቀዋል።

LEAVE A REPLY