የታከለ ኡማ ከከንቲባነት መነሳት ከቀበሌ እሰከ ክ/ከተማ በተሰገሰጉ ተረኞች ላይ ድንጋጤን ፈጥሯል

የታከለ ኡማ ከከንቲባነት መነሳት ከቀበሌ እሰከ ክ/ከተማ በተሰገሰጉ ተረኞች ላይ ድንጋጤን ፈጥሯል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ግልፅ የሆነ የመሬት ወረራ እንዲስፋፋና የ”ኬኛ” ፖለቲካ ሥር እንዲሰድ አይነተኛ ሚና ተጫውተዋል የሚባሉት ታከለ ኡማ ከም/ከንቲባነታቸው ተነሱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ዋና መዲናዋን በከንቲባነት ሲያገለግሉ የቆዮት ታከለ ኡማ ከሓላፊነታቸው ተነስተው፣ በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትርነት እንዲያገለግሉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል።
የታከለ ኡማ ከከንቲባነት መነሳት በኬኛ ፖለቲካ አራማጆችና  ሕገ ወጥ መሬት ወራሪዎች፣ በዘር ፖለቲካ በየክፍለ ከተማውና በየቀበሌው በተሰገሰጉ ተረኞች ዘንድ ከባድ ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፤ በአንጻሩ በተጠቀሱት ጊዜያት በአንድነት ተምሳሌት ከተማዋ የአንድ ብሔር የበላይነትን ለማስፈን ሙከራ መደረጉ ሲያሳዝናቸውና ሲያበሳጫቸው በቆዮ በርካታ የአዲስ አበቤ ነዋሪዎች ዘንድ ደስታን ፈጥሯል።
ከምክትል ከንቲባነታቸው የተነሱት ታከለ ኡማ  በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት፤ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ማገልገል ደስታ እንደሰጣቸውና የከተማዋን ችግሮች ለመቅረፍ የተቻላቸውን ማድረጋቸውን አስነብበዋል።
“አዲስ አበባን መምራት ትልቅ ዕድል ነው። ደጋግመን እንደምንለው፤ በታሪክ አጋጣሚ ያገኘነውን እድል ላለማባከን ጥረናል። በሁሉም ውስጥ የነዋሪዎቻችን ብርቱ ድጋፍ አብሮን ነበር። አዲስ አበባን እንደስሟ ለማድረግ በደስታ፤ በፍላጎትና በፍቅር ስንተጋ ምርኩዝ ለሆናችሁን ሁሉ፤ ከልቤ አመሰግናለሁ! በፍጹም ቅንነት ላጎደልናቸው ነገሮችም ይቅርታ እጠይቃለሁ” ሲሉም ስንብታቸ
ውን አውጀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የታከለ ኡማን ቦታ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግነት የተነሱት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሊይዙት እንደሚችሉ እየተነገረ ነው።

LEAVE A REPLY