ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ድንገተኛ ሹመቶችን ሰጡ

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ድንገተኛ ሹመቶችን ሰጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  ዛሬ ይፋ በሆነው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዐሥር ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በተለይም ከወራት በፊት የመለስ ዜናዊ አካዳሚን እንዲመሩ የቀረበላቸውን ሹመት አጥብቀው የተቃወሙት የቀድሞው የአዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ዮሐንስ ቧያለው ከፍተኛ ሹመት ማግኘታቸው ታውቋል።
በዚህም መሠረት የቀድሞ የአማራ ከልል ባለሥልጣን አቶ ዮሐንስ ቧያለው የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢኒስቲትዮት ዋና ዳይሬክተርነት ሹመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሰጥቷቸዋል።
በተያያዘ ዜና አቶ ተስፋዬ ዳባና ፍቃዱ ጸጋ በምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግነት፣  እንደአወቅ አብቴ፤ የብረታ ብረት ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ ፕሮፌሰር ኂሩት ወልደ ማርያም፤ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሆነው መሾማቸው ይፋ ሆኗል።
በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሓላፊ የነበሩት አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከነበሩበት ሓላፊነት ተነስተው የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ተሹመዋል።

LEAVE A REPLY