ለማ መገርሳ ከመካላከያ ሚኒስትርነት ተነስተው በምትካቸው ዶ/ር ቀንዓ ያደታ ተሹመዋል

ለማ መገርሳ ከመካላከያ ሚኒስትርነት ተነስተው በምትካቸው ዶ/ር ቀንዓ ያደታ ተሹመዋል

Office call in honor of His Excellency Lemma Mergesa, minister of defense, Democratic Republic of Ethiopia, hosted by Army Maj. Gen. Timothy Kadavy, special assistant to the chief of the National Guard Bureau, the Pentagon, Washington, D.C., Dec. 3, 2019. (U.S. Army National Guard photo by Sgt. 1st Class Jim Greenhill)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከሰሞኑ ከኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ አባልነታቸው የታገዱት፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ከሥልጣናቸው ተነስተዋል።

አቶ  ለማ ኢሕአዴግ ከስሞ፣ የብሔር አደረጃጀት ወደ አንድ ወጥ ፓርቲነት እንዲቀየርና የብልፅግና  ፓርቲ እንዲመሠረት የቀረበውን ሀሳብ በእጅጉ ያጣጣሉትና በኦዴፓ መፍረስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የተላተሙት ለማ መገርሳ በመሪነት ይዘውት ከመጡትና ሥልጣን ላይ ከወጣው የለውጥ ቡድን (ቲም ለማ) አስተሳሰብ ይልቅ በጽንፈኛ ኦሮሞ ብሔርተኞች ፍቅር ተይዘዋል በሚል  ሲታሙ ቆይተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ቀጥተኛና የተጠና ሹምሽር እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ አዳዲስ ዐስር ሹመቶችን ሰጥተዋል።
ሀገራዊ ወጥ ፓርቲ ከመመስረት ይልቅ የብሔር አደረጃጀቱን መርጠው ከትግል አጋሮቻቸው ጋር የተለያዩት አቶ ለማ መገርሳ ምትክ ፤ ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚንስትር ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY