በምዕራብ ጉጂ 32 የኦነግ ሸኔ አባላት እጅ ሰጡ

በምዕራብ ጉጂ 32 የኦነግ ሸኔ አባላት እጅ ሰጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 32 የኦነግ ሸኔ አባላት  እጃቸውን ሰጡ፡፡

የጉጂ ዞን ዋና አሰተዳደር አቶ ተፈሪ ወንድይፍራው መረጃ ከዚህ በፊት ዞኑ በጸጥታ ችግር ውሰጥ የቆየ ቢሆንም ዛሬ ላይ ግን ከህዝብ ጋር በተሠራ ሥራ 32 የኦነግ ሸኔ አባላት እጃቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
“የተሰጠን ተልዕኮ  በሀገር ደረጃ እየታየ ያለውን ለውጥ ማደናቀፍና የህዳሴውን ግድብ ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶችንና ንጹሐን ዜጎችን ማጥቃት ነበር ” ያሉት እጅ ሰጪዎች ከእንግዲህ በኋላ ልዮነታቸውን በሰላማዊ ትግል ለመቀጠል ማሰባቸውን ተናግረዋል።
አቶ ገልማ ቦሩ ወይም የትግል ስሙ ዲና ራሳ የተባለው የኦነግ ሸኔ አባል፤ ከስም አወጣጥ ጀምሮ ሕዝቡን እንዲገድል እና ጥፋት እንዲያደረስ ተልዕኮ እደተሰጠው ከመጠቆሙ ባሻገር፤ መሰረተ ልማቶችንና ንጹሐን ዜጎችን ለማጥቃት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ይፋ አድርጓል።
ሌላው የኦነግ ሸኔ አባል የሆነው አበበ ጂሎ ወይም አብዲ ሰባ ” እኔ አርሶ አደር ነበርኩ ፤ እነሱ በውሸት ሰብከው ወደነሱ ገብቼ ሥልጠናን በመውሰድ ተቀላቀልኩ፣ ተግባራቸው አስነዋሪ መሆኑን ተመልክቼ እጅ ሰጥቻለሁ” ብሏል።

LEAVE A REPLY