በሀገር ቤት የሚገኙ ባንኮች ዶላር ከውጭ እንዳይበደሩ የተጣው ገደብ ማንሳቱን ብሔራዊ ባንክ...

በሀገር ቤት የሚገኙ ባንኮች ዶላር ከውጭ እንዳይበደሩ የተጣው ገደብ ማንሳቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገር ቤት የሚገኙ ባንኮች ዶላር ከውጭ እንዳይበደሩ የጣለውን ገደብ ማንሳቱ ታወቀ።

የገደቡ መነሳት ዋና ምክንያት ከተለመደው አሠራር ወጣ ባለ መልኩ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ታልሞ እንደሆነም ተሰምቷል።
በኢትዮዮጵያ የወጭ ንግድ ቢሻሻልም የውጭ ምንዛሬ ግኝቱ በታሰበለት መጠን እንዳልተሳካም ይፋ ተደርጓል።
ይህንንም የውጭ ምንዛሬ ግኝት መላ ለማሳካት የሀገር ቤት ባንኮች ከውጭ የሚወስዱትን የውጭ ምንዛሬ ብድር የሚከለክለውን ህግ ማንሳቱን የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ አስታውቀዋል።
የውጭ ምንዛሬ የሚገኝበትን መንገድ ለማሻሻል ስለተፈለገ ገደቡን ማንሳት ግድ እንደሆነ የገለጹት የባንኩ ገዢ፣ የብሔራዊ ባንክ ለዚህ ሥራ ከፍተኛ ክትትል እና ቁጥጥር በየጊዜው ያደርጋልም ብለዋል።
ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎች እና ሌሎች ችግሮች እንዳይከሰቱ ይሠራል መባሉን ፣ እንዲሁም በዚሁ ጉዳይ ላይ ከባንኮች ጋር ውይይት መደረጉን ዶክተር ይናገር ደሴ ይፋ አድርገዋል።
በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከ 1.5 ሚሊዮን ብር በላይ በቤት ማስቀመጥ እንደማይቻልም የተገለጸ ሲሆን፤ የተከለከለውን 1.5 ሚሊየን ብር በላይ መያዝ በህግ እንደሚያስቀጣ፣ እንዲሁም የብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሥርዓት ኃላ ቀር በመሆኑ እና ዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን በማስፋት ወደ ሥራ እንዲገባ እንደሚደረግ መመርያ መውጣቱ ታውቋል።
በአዲሱ መመርያ መሰረት የ ኤ ቲ ኤም (ATM)፣ የፖስ(PoS) እና ሌሎች የክፍያ ሥርዓት ላይ ሌሎች ካምፓኒዎች የፋይናንስ ተቋም ባይሆኑም ወደ ሥራ መግባት ይችላሉ የተባለ ሲሆን፤ በ ATM፣ በPoS እና በሌላም የክፍያ ሥርዓት ከባንክ ውጭ ሌሎች ካምፓኒዎች የፋይናንስ ተቋም ባይሆኑም፣ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ወስደው “ባንክ ሳይሆኑ” እንዲሳተፉ እንደሚደረግም ገዢው አረጋግጠዋል።
እንዲህ አይነቱ አሠራር የዲጂታል ክፍያውን ጉዞ ያበረታታዋል የሚሉት ዶክተር ይናገር ደሴ፤ በዚህ ሥራ PoS Switch Gateway እና ATM ኦፕሬተርነት ለመሠማራት ማንኛውም ካምፓኒ የብሔራዊ ባንክን ፈቃድ ወስዶ መሥራት እንደሚችልም አብስረዋል።

LEAVE A REPLY