ጃዋር እንዴት ይታመማል? ሲሉ አደባባይ ከወጡ መሀል ሦስት ሰዎች ተገደሉ

ጃዋር እንዴት ይታመማል? ሲሉ አደባባይ ከወጡ መሀል ሦስት ሰዎች ተገደሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ለበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ነው የሚባለው ጃዋር መሐመድ ይፈታልን ያሉ ትናንት ከትናንት በስቲያ አመጽ ለመፍጠር የሞከሩና በአወዳይ ከተማ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይል ጋር ግጭት  ፈጠሩ።

ሰኞ እኩለ ቀን ላይ አቶ ጃዋር ታመዋል የሚለው ዜና መሰማቱን ተከትሎ፤ “ጃዋር መታከም አለበት፣ ከእስር መለቀቅም አለበት” የሚሉ መፈክሮችን የሚያሰሙ ወጣቶች መሰባሰብ እንደጀመሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት ሰዎችን ለመበተን ተኩስ እንደከፈቱ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
“አፍቃሪ ጃዋር የሆኑት ሰዎች መፈክር እያሰሙ ሰልፍ ለመውጣት ሲሞክሩ፣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና መከላከያ ሠራዊት ሰዎችን ማስቆም ጀመሩ። ከዛ ተኩስ ተከፍቶ ወደ 10 ሰዎች በጥይት ተመተዋል” በማለት ቃላቸውን ለቢቢሲ የሰጡ የዐይን እማኝ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መገደላቸውንም ይፋ አድርገዋል።
በተመሳሳይ እነዚሁ በስሜት የሚነዱ የመንጋ ቡድን አባላት ማክሰኞ እለትም (ትናንት) በአወዳይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርጉም የጸጥታ ኃይሉ ከአደባባይ ሳይደርሱ በየአካባቢያቸው መልሷቸዋል።
“ከ4 ሰዓት ጀምሮ ሰልፍ ሲካሄድ ነበር፤ በሽር የሚባል አካባቢ ተኩስ ተከፍቶ አንድ ሰው ተገድሏል። ከተማው አሁን ጸጥ ብላለች። የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም። ሱቆችም ዝግ ናቸው” ያሉት የአወዳይ ነዋሪ ዛሬ በአንጻሩ ምንም ዓይነት የአመፅ ሙከራ ባይደረግም፣ ከተማዋ ጸጥ ረጭ ብላ መዋሏን ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY