በድሬደዋ ሁለት ሰዎች በጥይት ሲገደሉ፣ ዐራት ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸው ታወቀ

በድሬደዋ ሁለት ሰዎች በጥይት ሲገደሉ፣ ዐራት ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸው ታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  የጃዋር መሐመድና የእነ ሐምዛ ቦረና ጽንፍ የያዘ ፖለቲካን የሚያራምዱ ግለሰቦች    በድሬደዋ ከተማ ዛሬም አመፅ ለመቀስቀስ ሙከራ ተደርጎ የነበረም መከላከያ ሠራዊት አካባቢውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉ ተገለጸ።

ትናንት በከተማዋ ጃዋር ይፈታ የሚሉ ኹከት ናፋቂዎች ረብሻ ለመፍጠር መሞከራቸውን የተናገረው የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን፤ በከተማዋ ከተከሰተው ሁከት እና ረብሻ ጋር ተያይዞ የሁለት ሰው ሕይወት ማለፉን፣ እንዲሁም በዐራት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰ በይፋ አረጋግጧል።
 “እኩይ አላማን ያነገቡ ኃይሎች ሰላማዊው ኅብረተሰብ ውስጥ ተሸሽገው፣ 12.12.12 በሚል ከውጪ የተሰጣቸውን የጥፋት ተልዕኮ ለማስፈጸም ላይ ታች ሲሉ የዋሉና የጣሩ ቢሆንም፤ በጸጥታ ኃይላችን እና በሰላም ወዳዱ የከተማችን ነዋሪ ጥረት የጥፋት ድግሳቸውን መና አድርጎ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል” ሲልም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY