በጭሮ ከተማ 23 ሰዎች በጥይት መመታታቸው ተሰማ

በጭሮ ከተማ 23 ሰዎች በጥይት መመታታቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በተለያዮ የሽብር ወንጀሎች ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የሚገኘው የአቶ ጃዋር መሐመድ ታመምኩ ሲል ፍርድ ቤት መናገሩን ተከትሎ ደጋፊዎቹ  ትናንት እና ሰኞ እለት በጭሮ ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ ግጭት ተከስቶ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል ተባለ።

ጉዳዮን አስመልክቶ ለቢቢሲ መረጃ የሰጡት የጭሮ ሆስፒታል ተጠባባቂ ሜዲካል ዳይሬክተር  ዶ/ር ሳዳም አሉዋን በጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታላቸው ከመጡ 24 ሰዎች መካከል የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል ብለዋል።
“በጥይት ተመትተው የመጡ ሰዎች አሉ፤ አጠቃላይ ቁጥራቸው 24 ሲሆን ፣ ከእነዚህ መካከል የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል” ያሉት የሆስፒታሉ ዳይሬክተር፤
ከሞቱት መካከል አንዷ በ40ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ትልቅ ሴት ስትሆን፣ የተገደለችውም ጀርባዋን ተመትታ መሆኑን አብራርተዋል።
ሁለተኛው ሟች በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኝ ወጣት ወንድ እንደሆነና እርሱም ከጀርባው በጥይት የተመታ መሆኑን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት አንድ በጽኑ የተጎዳ ወጣት ለተጨማሪ የሕክምና እርዳታ ወደ አዳማ የተላከ ሲሆን፣ ከቀሪዎቹ መሀል አብዛኛዎቹ እጃቸውን እና እግራቸውን የተመቱ፣ እንዲሁም የአጥንት መሰበር ያጋጠማቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
 በጭሮ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የጃዋር ደጋፊዎች፤ ከትናንት በስቲያ ከሰዐት 11 ሰዓት አካባቢ ቀበሌ 03 ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ግጭት የቀሰቀሱ ሲሆን፤
ትናንትም በተመሳሳይ በጭሮ ዙሪያ ከሚገኙ መንደሮች ብዙ የመንጋ አባላት ለተቃውሞ ወደ ጭሮ ከተማ በሚመጡበት ወቅት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ሰዎቹን ተኩስ በመክፈት እንደበተኗቸው ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY