449 ሺኅ 700 ዶላር (17 ሚሊዮን ብር) በሁመራ በኩል ከሀገር ሊወጣ ሲል...

449 ሺኅ 700 ዶላር (17 ሚሊዮን ብር) በሁመራ በኩል ከሀገር ሊወጣ ሲል ተያዘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  449 ሺኅ 700 የአሜሪካ ዶላር ከሀገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተነገረ።

ከፍተኛ የሆነ የኮንትሮባንድ እቃዎች  በሚንቀሳቀስበት ሁመራ መስመር በሦስት የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ከላይ የተገለጸውን ብር ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከሩ ነው ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ለመያዝ የተቻለው።
አሁን ላይ ባለው የዶላር ምንዛሪ ተመን 17.8 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው ይህ ገንዘብ፣ እንዲሁም በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የተጠረጠሩት ሦስት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉም ታውቋል።
ግለሰቦቹ ገንዘቡን ከሀገር ለማስወጣት የሞከሩት በሁመራ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ፣ የሊጉዲ መቆጣጠሪያ ጣቢያን ወደ ጎን በመተው በጫካ በመጓዝ እንደሆነም መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሩን በመከታተልና በመያዝ የሁመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ሠራተኞች፣ የመከላከያ ሠራዊት እና ፌዴራል ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ሲሆን፣ የተያዘው ገንዘብም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ተደርጓል፡፡

LEAVE A REPLY