ኮሮና ቫይረስ በሁለት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠፋ WHO አሳወቀ

ኮሮና ቫይረስ በሁለት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠፋ WHO አሳወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና  የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ኢትዮጵያዊው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም ገለጹ።

ስፓኒሽ ፍሉ በጎርጎሮሳውያኑ 1918 በተከሰተበት ወቅት ለመጥፋት የወሰደበት ጊዜ ሁለት ዓመት እንደነበር ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤  ዓለም አሁን ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ መራቀቅና ከፍተኛ ምርምሮች አንጻር የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ ይችላል ብለዋል።
በአንጻሩ አሁን ባለው ከፍተኛ የሰዎች ማኅበራዊ ትስስር ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀመጡት  ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም፤ ”ነገር ግን የሰው ልጅ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ርቀት ቫይረሱን ለማስቆም የሚረዳ እውቀት በቶሎ እንዲያዳብር ይረዳዋል”  ሲሉም ተስፋቸውን ገልጸዋል።
በ1918 (በጎርጎሳውያን አቆጣጠር) የተከሰተው ስፓኒሽ ፍሉ በጥቂቱ 50 ሚሊየን ሰዎችን ሲገድል፤ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 800 ሺኅ እንደደረሰና ዓለም ላይ በአጠቃላይ 22.7 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ከመግለጫው መረዳት ተችሏል
 የግል መከላከያ መሳሪያዎች ወይም ‘ ፒፒኢ ሥርጭትን በተመለከተ ሙስና እየተስተዋለ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ” ይሄ ወንጀል ነው፤ ማንኛውም አይነት ሙስና ተቀባይነት የለውም። ከፒፒኢ ጋር የተያያዘ ሙስና ለእኔ በግሌ እንደ ነብስ ማጥፋት ነው የምቆጥረው። ምክንያቱም የጤና ባለሙያዎች ፒፒኢ የማያገኙ ከሆነ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣልን ነው። በተጨማሪም የሚያገለግሏቸው ሰዎችን ሕይወትም ነው ስጋት ውስጥ የምንከተው” ሲሉ በዘርፉ የሚስተዋለውን ሕገ ወጥ አካሄድ በእጅጉ ኮንነዋል።

LEAVE A REPLY