በጎንደር ታች አርማጭሆ ሰው በማገት የተጠረጠረ ወንጀለኛ በ12 ዓመት እስራት ተቀጣ

በጎንደር ታች አርማጭሆ ሰው በማገት የተጠረጠረ ወንጀለኛ በ12 ዓመት እስራት ተቀጣ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ሰው ማገት ወንጀል ክስ ተመስርቶበት የነበረ ግለሰብ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

የአካባቢው ዐቃቤ ህግ ጽሕፈት ቤት ተወካይ አቶ ጌታሁን ታከለ ፤ የእስራት ቅጣቱ ውሳኔ የተላላፈበት ናቃቸው ተዘራ የተባለ የሙሴ ባንብ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን፣ ግለሰቡ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ካን ፈንታ በተባለው ቀበሌ ካገተው ግለሰብ 20 ሺኅ ብር አስከፍሎ መልቀቁ  የሰውና የሰነድ ማስረጃ እንደተረጋገጠበት አስታውቀዋል።
ተከሳሹ ድርጊቱን አልፈጸምኩም ብሎ ክዶ ቢከራከም በዐቃቤ ህግ ምስክሮች በመረጋገጡ ፤ የሙሴ ባንብ ንዑስ ወረዳ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል።
ተከሳሹ ከአራት ዓመት በፊት በስርቆት ወንጀል ተከሶ የእስራት ጊዜውን አጠናቆ ከወጣ በኋላ በድጋሚ የሰው እገታ ወንጀል በመፈጸሙ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን በቅጣት ማክበጃነት ይዞበታል ያሉት ሓላፊው፤ ተከሳሹ ፈጽሟል በተባለው የሰው እገታ ወንጀል ጥፋተኝነቱ በመረጋገጡም ፍርድ ቤቱ ትናንት በዋለው ችሎት እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ የእስራት ቅጣት ውሳኔውን እንዳስተላለፈ አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY