የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎቹን ለመሸጥ ዓለም ዐቀፍ ጨረታ አውጥቻለሁ አለ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎቹን ለመሸጥ ዓለም ዐቀፍ ጨረታ አውጥቻለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ዝቅተኛ የሆነ የኳስ ደረጃ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዓለም ዐቀፍና የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት ጨዋታዎችን ማስተላለፍ እንዲችሉ ጨረታ አውጥቻለሁ አለ።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ፤ ማኅበሩ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን ለመሸጥ አቅዶ ጨረታ ማውጣቱን ይፋ አድርገዋል።
 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን በቴሌቪዥን ለማሰራጨት የብሮድካስቲንግ መብቱን ለመሸጥ በማሰብ የዓለም ዐቀፍ እና የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃኖች እንዲወዳደሩ ጨረታ ማውጣቱን የገለጹት ሓላፊው፤
በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ኩባንያ የሚጠራበትን ስም ለመሸጥ ጨረታ እንደወጣም አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ 16 ቡድኖች በጋራ ያቋቋሙትና በንግድ ድርጅትነት የተመዘገበ ማኅበር መሆኑኑንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
 በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምከንያት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዝግ ስታድየም የሚታይ ከሆነ፤ ወይም ምርመራ እንዲደረግ ግዴታ የሚቀመጥ ከሆነ ተጨማሪ ወጪ ስለሚጠይቅ እነዚህን ነገሮች ለመሸፈን በማሰብ የተለየ አማራጭ መታሰቡንም ሓላፊው አብራርተዋል።
ከሚዲያ ሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ የአክሲዮን ማኅበሩ አባል ቡድኖች ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቀው ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ፣ እንዲሁም በአፍሪካም ሆነ በአውሮፓ ደረጃ ያሉ የስፖርት ቡድኖች እንደሚያደርጉት የስፖርት ኢንቨስትመንት ውስጥ እንዲገቡ መነሻ ሊሆናቸው ይችላል ተብሏል።
ከጨረታው የሚገኘው አብዛኛው ገቢ የሚሰጠው ለእግርኳስ ቡድኖቹ ሲሆን፣ ቀሪው የድርጅቱ ሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል ተብሏል።

LEAVE A REPLY