ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮና የኦፌኮ ዋና ጸሐፊ ደጀኔ ጣፋ በዋስ እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ...

ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮና የኦፌኮ ዋና ጸሐፊ ደጀኔ ጣፋ በዋስ እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ ወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት አቶ ደጀኔና ጋዜጠኛ ጉዮ በዋስ ከእስር እንዲወጡ መወሰኑ ተሰማ።

የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፤ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ እና ከእርሳቸው ጋር በአንድ መዝገብ ችሎት የቀረቡ ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች በ10 ሺኅ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ዛሬ ብይን ሰጥቷል።
በተያያዘ ዜና በሌላ የክስ መዝገብ ዛሬ ችሎት የቀረበው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ በተመሳሳይ የዋስትና የገንዘብ መጠን (10,000 ብር) ከእስር እንዲወጣ መበየኑን ለማወቅ ተችሏል።
ጋዜጠኛ ጉዮ ዋርዮ ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ከመሞቱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በኦ ኤም ኤን ቴሌቪዥን ላይ የሰጠውን አነጋጋሪ ቃለምልልስ ያደረገው መሆኑን አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY