የአምባሳደሮቸ ስብሰባ በቢሾፍቱ ከተማ ተጀመረ፣ በቀጠዮቹ ሳምንታት አዳዲስ ሹመቶች ይኖራሉ

የአምባሳደሮቸ ስብሰባ በቢሾፍቱ ከተማ ተጀመረ፣ በቀጠዮቹ ሳምንታት አዳዲስ ሹመቶች ይኖራሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዓመታዊው የአምባሳደሮች ጉባዔ ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ እየ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

“ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎችን ለአገራዊ ብልፅግናችን’’ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የአምባሰደሮች ጉባዔ ላይ፤ የዋናው መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሚሲዮን መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች መሳተፋቸው ተሰምቷል።
ዛሬ በተጀመረው ጉባዔ መክፈቻ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሃገሪቱ በ2012 ዓ.ም ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በመተግበር ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ለተሳታፊዎች አስረድተዋል።
ጉባዔው በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በተከለሰዉ ረቂቅ የውጭ ጉዳይ ደህንነት ፖሊሲ እና ሃገራዊ ለውጥ  ዙሪያ ግምገማና ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
በተለያዮ ሀገራት የሚገኙ አምባሳደሮችና ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች ከአርብ እለት ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ የሚጠቁሙ ታማኝ ምንጮች ከጉባዔው መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት ውስጥ በአምባሳደርነት ደረጃ የተለያዮ ሹመቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊኖር እንደሚችል ጭምጭምታዎች መኖራቸውን ገልጸውልናል።

LEAVE A REPLY