ስምንት የኦነግ ሸኔ ከምፕ ተደመሰሰ፤ የታጣቂዎቹ አዛዦች ለሁለት ተከፍለው እርስ በርስ ተዋጉ

ስምንት የኦነግ ሸኔ ከምፕ ተደመሰሰ፤ የታጣቂዎቹ አዛዦች ለሁለት ተከፍለው እርስ በርስ ተዋጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በመከላከያ ሠራዊት አማካይነት ከፍተኛ ጥቃት እየተፈጸመበት ያለው የኦነግ ሸኔ ጦር ለሁለት እንደተከፈለ መረጃዎች እየወጡ ነው።

በደቡብ ኦሮሚያ ቦረና አካባቢ የሚገኘው የኦነግ ሸኔ ጦር በሁለት ተከፍሎ ከባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ እርስ በራስ  ሲዋጋ መሰነበቱሞ ተሰምቷል።
በዚህ የኦነግ ሸኔ አባላት የእርስ በርስ ውጊያ ከሁለቱም በኩል በርከት ያሉ ታጣቂዎች መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል። በቦረና አካባቢ ባሉ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ወደ ዋናው የኦነግ ሸኔ መፈልፈያ  ምእራብ ወለጋና ምስራቅ ጎጃም እንዳይዛመት በአባሎቹ ዘንድ ሥጋት ተፈጥሯል።
በምእራብ ወለጋ ያለው የኦነግ ሸኔ ጦር በጃል መሮ የሚመራ ሲሆን፣ ይህ ታጣቂ ቡድን በአሁኑ ሰዐት ከመከላከያ ሠራዊት የሚደርሰበትን ጥቃት መቋቋም አቅቶት በአስፈሪውና ሠፊው የወለጋ ጫካ ውስጥ እንደተደበቀ የሚጠቁሙ መረጃዎች፤ የእዚህ ጦር አዛዥ የሆነው ጃል መሮ በሰሞነኛው ጥቃት ተገድሏል በሚል የሚናፈሱት ዜናዎች ከእውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በቦረና የሚገኘው የእነግ ሸኔ ጦር መሀል የተከሰተውና ለእርስ በርስ ጦርነት ያበቃው ክፍፍል በጦር መሪው በጃል ጎልቻ ድሂንጎ ጎዳናና በምክትሉ ገመቹ አቦዬ መካከል እንደሆነም ታውቋል።
ጃል ጎልቻ ሸሽቶ ጥቂት ታጣቂዎችን ይዞ ሲአሎ ገብቶ የነበረ ቢሆንም ትናንት ወደ ሶሎሎ ሙካታኖ ተመልሶ በመጣበት ወቅት የዋና አዛዡ የገመቹ ቡድን ቁጥጥር ሥር እንዳዋለዉ በመነገር ላይ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንትበቦረና ዞን ድሬ ወረዳ መጋዶ ቀበሌ ልዩ ስሙ አላ ዲምቱ አካባቢ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በኦነግ ሸኔ ጦር ላይ ባደረሰው ጥቃት ስምንት ያህል የኦነግ/ሸኔ ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን፤ በጦርነቱ ከተገደሉት ውጥ አንድ ሴት ቆስላ ተማርካ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ሕይወቷ ማለፉ ተረጋግጧል።
በተመሳሳይ በሚዮ ወረዳ ደግሞ 4 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሲገደሉ ፣ ሁለት መያዛቸውንና ሠባቱ መቁሰላቸውን የተናገሩ ምንጮቻችን፤ በሞያሌ  2  የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሲያዙ፣ አራት መገደላቸውን ገልጸዋል።
በሰሞነኛ የመከላከያ ሠራዊት ጥቃት በአጠቃላይ 8 የኦነግ ሸኔ ካምፕ መደምሰሱን ከተለያየ አቅጣጫ የሚወጡት መረጃዎች ያሳያሉ።

LEAVE A REPLY