ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፉት ሃያ ሥድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝቦች መካከል በርካታ ችግሮችን እየፈጠረ ያለውና በህወሓት ቀጥተኛ ፍላጎት የፀደቀው ሕገ መንግሥት እንዲሻሻል ብዙኃኑ ከፍተኛ ፍላጎት አለው ተባለ።
ከኢትዮጵያ ሕዝብ መሀል 69 በመቶ ኢትዮጵያዊያን የሕገ መንግሥት መሻሻልን የሚደግፉ ሲሆን፤ 11 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሌላ እንዲተካ ፍላጎት አላቸው ተብሏል።
በአንጻሩ 43 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ከአወዛጋቢው ሕገ መንግሥት ውስጥ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እሰከመገንጠል ድረስ የሚፈቅደው አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ፍላጎት እንዳላቸው ተሰምቷል።
ተደረገ በተባለው ጥናት መሠረት የሕገ መንግሥት መሻሻልን የሚደግፉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር 69 በመቶ ሲሆን፤ 11 በመቶ ሚሆኑት ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሌላ ይቀየር ባይ ናቸው።
18 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ደግሞ በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት ባለበት እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላቸው በጉዳዮ ላይ ሠፊ ጥናት ያካሄደው አፍሮ ባሮሜትር የተሰኘው ተቋም አስታውቋል።
የጥናት ግኝቱ 43 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ከሕገ መንግሥቱ ላይ “ነቀርሳ” ነው ያሉት አንቀጽ 39ኝ እንዲሰረዝ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውም አረጋግጧል።