በዐቢይ አሕመድ የተሾሙት የፋና ሥራ አስኪያጅ በሙስና ተጠርጥረው ከሓላፊነታቸው ተነሱ

በዐቢይ አሕመድ የተሾሙት የፋና ሥራ አስኪያጅ በሙስና ተጠርጥረው ከሓላፊነታቸው ተነሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከወራት በፊት የፋና ቴሌቪዥንና ራዲዮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመው የነበሩት ግለሰብ ከሓላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉ ተሰማ።

የቀድሞው ኦህዴድ (አዴፓ) አባል የሆኑት እና ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት  ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ በቀለ ሙለታ ባላቸው የካበተ ልምድ አማካይነት ተመርጠው በቅርቡ  የፋና ፕሮዳክሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንዲሆኑ ተሹመው ሥራቸውን ሢሠሩ ነበር።
ለበርካታ ዓመታት የህወሓት ልሳን፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ የለውጡ ቡድን የፕሮፐጋንዳ መገልገያ የሆነው ፋና ኮርፖሬትን ለወራት በሓላፊነት የመሩት ግለሰቡ ድንገት ከሓፊነታቸው የመነሳታቸው ምክንያት ከሙስና ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተሰምቷል።
አቶ በቀለ ሙለታ ፋናን ከመረከባቸው በፊት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርነት ላይ እያሉ ፈጽመውታል በሚል የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ምክንያት አሁን ከነበሩበት ቦታ እንዲነሱ ተደርገዋል የሚሉት ታማኝ ምንጮች ጉዳያቸው በጸረ ሙስና ኮሚሽን እንደተያዘም ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY