ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ግዙፉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከመጥፎ ምግባር ጋር በተያያዘ 75 ሠራተኞችን ማሰናበቱ ተሰማ።
ተቋሙ በብልሹ አሠራር ተሳትፈዋል፣ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የሥነ-ምግባር ችግር ታይቶባቸዋል ያላቸውን 75 ሠራተኞች ከሥራ ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጥቅሉ 305 ሠራተኞቹ ላይ የተለያዩ የቅጣት እርምጃዎችን እንደወሰደም አስታውቋል።
ከእነዚህ ውስጥ 75ቱ ሠራተኞች ከሥራ ሲሰናበቱ፣ 219ኙ ደግሞ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል። እንደ ተቋሙ መግለጫ ከሆነ 11 ሠራተኞች የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
የቅጣት እርምጃ የተወሰደባቸው፤ 44 ሓላፊዎች፣ 147 ቴክኒሺያኖች፣ 22 ቆጣሪ አንባቢዎች፣ 10 የስቶር ሠራተኞች፣ 19 አሽከርካሪዎች እና 13 ገንዘብ ያዦች መሆናቸውም ታውቋል።