ኢትዮ ቴሌኮም በኢንተርኔት ጥቅል አገሌግሎት ላይ 35 በመቶ ቅናሽ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም በኢንተርኔት ጥቅል አገሌግሎት ላይ 35 በመቶ ቅናሽ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  በኢትዮጵያ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ሆነው ከፍተኛ ትርፍ ከሚያጋብሱት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም የዋጋ ማሻሻያዎችን አደረገ።

በዚህ መሠረት ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት ላይ  እስከ 35 በመቶ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን፣ በቤትዎ ይቆዮ የጥቅል አገልግሎትም 59 በመቶ ቅናሽ ተደርጎለታል።
በተመሳሳይ የድምፅ ጥቅል አገልግሎት ላይም  የ29 በመቶ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን ፤ አገልግሎቱም  ከነገ ነሐሴ 21/2012 ጀምሮ በሥራ ላይ እንደሚውል ተሰምቷል።
በተጨማሪም እስከ 11 የሚደርሱ ሀገራት ላይ የውጭ ጥሪ አገልግሎት 50  በመቶ ቅናሽ የተደረገ መሆኑን ተቋሙ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ከውጭ ዓለም አቀፍ ጥሪ ለሚቀበሉ ደንበኞች ከኢትዮ ቴሌኮም ስጦታ እንደሚበረከትላቸውም ታውቋል።

LEAVE A REPLY