184 ባለሥልጣናት ሀብታቸውን ባለማስመዝገባቸው ክስ እንዲመሰርትባቸው ስማቸው ለፖሊስ ተላለፈ

184 ባለሥልጣናት ሀብታቸውን ባለማስመዝገባቸው ክስ እንዲመሰርትባቸው ስማቸው ለፖሊስ ተላለፈ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሀብት መጠናቸውን አናስመዘግብም ያሉ የበርካታ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስም ዝርዝር ለፌደራል ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ ተሰማ።

በሀገሪቱ የሚገኙ ባለሥልጣናትና ከፍተኛ አመራሮች ያካበቱትን የሀብት መጠን እንዲያሳውቁ ወይም እንዲያስመዘግቡ የወጣውን መመሪያ ተከትሎ በርካታ ባለሥልጣናት የሀብት መጠናቸውን ሲያስመዘግቡ ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ አሠራሩን እንዲተገብሩ ቢጠየቅም አፈጻጸም ላይ ወደ ኋላ የቀሩና የሀብት መጠናቸው ያልተመዘገበ ባለሥልጣናት ላይ በቅርቡ ክስ ሊመሠረት ይችላል ተብሏል።
በዚህ መሠረት የፌደራል ሥነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ያልሆኑ 184 ባለሥልጣናት በወንጀል እንዲከሰሱ ስም ዝርዝራቸውን ለፌደራል ፖሊስ ሰጥቻለሁ ሲል አረጋግጧል።
ክስ ይመሰርትባቸዋል የተባሉት እነዚህ 184 ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ መቼ ክሱ እንደሚጀምር ባይታወቅም  የባለሥልጣናቱ ስም ዝርዝር  ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY